“የኢትዮጵያ መንግሥት አጠቃላይ ገቢ ባለፉት ሰባት ዓመታት በ446 በመቶ ዕድገት አስመዝግቧል” - የገንዘብ ሚኒስትር
16:41 16.01.2026 (የተሻሻለ: 16:44 16.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
“የኢትዮጵያ መንግሥት አጠቃላይ ገቢ ባለፉት ሰባት ዓመታት በ446 በመቶ ዕድገት አስመዝግቧል” - የገንዘብ ሚኒስትር
ከአጠቃላይ የመንግሥት ገቢ ውስጥ የታክስ ገቢ በ400 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ተናግረዋል።
መንግሥት በሁለት ምዕራፍ ተግባራዊ ያደረጋቸው የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራሞችን ተከትሎ ባለፉት ሰባት ዓመታት ውስጥ 25 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ማሰባሰብ መቻሉን ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።
እንደ ሚኒስትሩ ገለፃ፦
ለድህነት ተኮር ዘርፎች የተመደበው በጀት ከ2010 ዓ.ም አንጻር በአራት እጥፍ አድጓል።
በ2010 ዓ.ም. 2.5 በመቶ የነበረው የበጀት ጉድለት በ2017 ዓ.ም. ወደ 0.9 በመቶ ዝቅ እንዲል ተደርጓል።
ይህ ስኬት የተመዘገበው መንግሥት ጠንካራና ዘመናዊ ተቋማትን በመገንባት እንዲሁም ቀልጣፋ የገቢ አሰባሰብ ስልቶችን በመቀየሱ መሆኑን ሚኒስትሩ አክለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X