የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ታሪካዊ ነው የተባለ የ2.1 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማስመዝገቡ ተገለፀ
15:35 16.01.2026 (የተሻሻለ: 15:44 16.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ታሪካዊ ነው የተባለ የ2.1 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማስመዝገቡ ተገለፀ
ባለፉት ስድስት ወራት የተገኘው ይህ ገቢ፤ በታሪክ የመጀመሪያው እንደሆነ የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን የሚያስተዳድረው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ብሩክ ታዬ ተናግረዋል።
ለትርፉ መመዝገብ የጎላ ድርሻ አላቸው ተብለው የተጠቀሱ ጉዳዮች፦
🟠 ተቋሙ የነበረበት ከፍተኛ የብድር ጫና ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መተላለፉ፣
🟠 በመንግሥት የተተገበረው የኢኮኖሚ ሪፎርም፣
🟠 የታሪፍ ማሻሻያ፡፡
“አሁን ላይ የተመዘገበው ትርፍ ተቋሙ ካለበት የብድር ጫና ወጥቶ ራሱን እንዲችል መንገድ የሚከፍት ነው” ሲሉም ዋና ሥራ አስፈፃሚው ጠቁመዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X