አፍሪካ በማስፈራሪያ ብሪክስን እና ሩሲያን ልትተው አትችልም - ካሜሩናዊ የፖለቲከ ፍልስፍና ባለሙያ

ሰብስክራይብ

አፍሪካ በማስፈራሪያ ብሪክስን እና ሩሲያን ልትተው አትችልም - ካሜሩናዊ የፖለቲከ ፍልስፍና ባለሙያ

አሜሪካ 26 የአፍሪካ ሀገራትን ጨምሮ በ75 ሀገራት ላይ የኢሚግሬሽን ቪዛ ለማቆም መወሰኗ ለአፍሪካ እንደ እንቅፋት ሳይሆን እንደ አዲስ ምዕራፍ ሊታይ ይገባል ሲሉ የ "ኬፐር" ምርምር ተቋም መስራች ያምብ ንቲምባ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

ይህ ፖሊሲ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለውን የኃይል አለመመጣጠን የሚያጋልጥ፤ የአፍሪካ ሀገራትም ስለ ወደፊት እጣ ፈንታቸው ዳግም እንዲያስቡ ዕድል የሚፈጥር ነው ሲሉ ንቲምባ አስረድተዋል።

የአፍሪካ አንድነት ይበልጥ እንዲጠናከር የጠየቁት የፖለቲካ ባለሙያው፤ የቪዛ እገዳው የሚመለከታቸው ሀገራት ተባብረው የፌደራል ዓይነት ጥምረት ቢፈጥሩ በጥቂት አሥርተ ዓመታት ውስጥ በዓለም ላይ ትልቅ ኃይል መሆን እንደሚችሉ ጠቁመዋል።

“ስለ ጥንካሬያችን እንወቅ፤ ስለ ኃይላችን እንገንዘብ። ይህንንም አማራጭ ዓለም ለመፍጠር እንጠቀምበት” ብለዋል።

ንቲምባ ብሪክስን እንደ አማራጭ የዕድገት ማዕከል ጠቅሰው፤ አፍሪካ በምዕራባውያን ላይ ጥገኛ ከመሆን ይልቅ በእስያና ባሻከር ከታዳጊ ኢኮኖሚዎች ጋር ያላትን ግንኙነት ማጠናከር እንዳለባት ገልጸዋል።

የአሜሪካ የቪዛ ገደብ ፖሊሲ የረጅም ጊዜ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል አስጠንቅቀዋል። በተለይም ዘረ አፍሪካውያን ለአሜሪካ ኢኮኖሚና ፈጠራ ትልቅ ሀብት መሆናቸውን ጠቁመዋል።

“ይህ የስትራቴጂ ጥያቄ ነው፡፡ የሀገሪቱን የወደፊት ዕይታ እና ከውጭው ዓለም ጋር የሚኖራትን ግንኙነት የሚመለከት ጉዳይ ነው” ብለዋል።

ንቲምባ አክለውም የቪዛ እገዳው አፍሪካውያን እንደ ቻይና፣ ሩሲያ እና ብሪክስ ካሉ አጋሮቻቸው እንዲርቁ ለማድረግ ከሚደረግ ሰፊ ጫና ጋር የተያያዘ መሆኑን ጠቁመው፤ ይህ ግን እውን ሊሆን የማይችልና ጎጂ መሆኑን ገልጸዋል።

↗ ይልቁንም በአፍሪካ ሀገራት መካከል ያለውን ንግድ ማሳደግ፣ የኢንዱስትሪ ልማትን ማፋጠን፣ ጥሬ ዕቃዎችን በሀገር ውስጥ ማቀነባበር እና በወጣቶች ላይ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ እንደሚገባ ሞግተዋል።

“ዓለም በጣም ሰፊ ናት” ያሉት ንቲምባ፤ አሜሪካ ለዘላቂ ዕድገት ብቸኛዋ መንገድ እንዳልሆነች አስረግጠዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0