ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በዶሃ ማራቶን በሁለቱም ጾታዎች አሸነፉ

ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በዶሃ ማራቶን በሁለቱም ጾታዎች አሸነፉ

በወንዶች ምድብ የተካሄደውን ውድድር የኦሎምፒክ ሻምፒዮኑ አትሌት ታምራት ቶላ፤ በ2 ሰዓት ከ5 ደቂቃ 40 ሴኮንድ የቦታውን ክብረ ወሰን በማሻሻል አሸንፏል።

ታምራትን በመከተል አትሌት አሰፋ ቦኪ ሁለተኛ፤ ቦኪ ዲሪባ ሶስተኛ፣ ድንቃለም አየለ አራተኛ እንዲሁም ባለው ይሁኔ አምስተኛ ደረጃን በመያዝ በውድድሩ ላይ የኢትዮጵያን የበላይነት አሳይተዋል።

በሴቶች ምድብ አትሌት ትዕግስት ገዛኸኝ ውድድሯን በቀዳሚነት ያጠናቀቀች ሲሆን፤ ሌላኛዋ አትሌት ትዕግስት ግርማ ሁለተኛ እንዲሁም ሙሉሀብት ጸጋ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ የዶሃ ማራቶንን በበላይነት አጠናቀዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0