ላይቤሪያ ኢንቨስትመንት እንጂ የማዕድናት የትግል አውድማ መሆን አትፈልግም - ሚኒስትር
ላይቤሪያ ኢንቨስትመንት እንጂ የማዕድናት የትግል አውድማ መሆን አትፈልግም - ሚኒስትር
ላይቤሪያ በዓለም አቀፉ የወሳኝ ማዕድናት ፉክክር ውስጥ ክፍት እና ገለልተኛ መዳረሻ ለመሆን እየሠራች መሆኗን እና ከጂኦፖለቲካዊ ሽኩቻ ይልቅ ለኢንቨስትመንት፣ ለተጨማሪ እሴት እና ለመረጋጋት ቅድሚያ እንደምትሰጥ የማዕድን እና ኢነርጂ ሚኒስትር ማቲኖካይ ቲንግባን ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
ላይቤሪያ ዓለም አቀፋዊ የፖለቲካ ግጭቶች መድረክ እንዳትሆን በመጠንቀቅ ኢንቨስትመንቶችን መሳብ ዋነኛ ፍላጎቷ ነው ሲሉ ሚኒስትሩ በሳዑዲ አረቢያ ሪያድ ከተካሄደው ከፊውቸር ሚነራልስ ፎረም ጎን ለጎን ገልፀዋል።
“የእኛ [ሀብት] ለፖለቲካዊ ዓላማ ብቻ እንዲፈለግ አንሻም ” ሲሉ ያስጠነቀቁት ሚኒስትሩ፤ በላይቤሪያ መሬት በማዕድን ዙሪያ ያተኮረ የኃይል ሽኩቻ የሀገሪቱን ልማት ያደናቅፋል ብለዋል።
ዝርዝር የጂኦሎጂ ጥናቶች እና የጂኦ-ሳይንሳዊ መረጃዎች ባለመኖራቸው ምክንያት የላይቤሪያ የማዕድን አቅም በአብዛኛው ሳይነካ በመቆየቱ፤ ሀገሪቱ ከማዕድን የተሻለ እሴት እንዳታገኝ ገድቧታልም ሲሉ አክለዋል።
ይህንን ለመለወጥ መንግሥት በሩን ለባለሀብቶች ክፍት በማድረግ፣ የኢንቨስትመንት ሁኔታዎችን በማጠናከር እና የይዞታ ደህንነትን በማረጋገጥ ላይ ትኩረት አድርጓል ብለዋል።
ጥሬ ዕቃዎችን በቀጥታ ወደ ውጭ መላክ የሀገሪቱን ገቢ እና የሥራ ዕድል ፈጠራ እንደገደበውም ጠቅሰዋል።
ሚኒስትሩ አክለውም ላይቤሪያ በራሷ ቅደመ ሁኔታዎች ላይ ተመስርታ ሁሉንም አጋሮች በእኩልነት እንደምትቀበል አፅንዖት ሰጥተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X