ቻይና የቀረጥ መሰናክሎችን በማንሳት ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የንግድ ልውውጥ እንዲቀላጠፍ እያደረገች ነው - ቡና ላኪ
11:02 16.01.2026 (የተሻሻለ: 11:04 16.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ቻይና የቀረጥ መሰናክሎችን በማንሳት ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የንግድ ልውውጥ እንዲቀላጠፍ እያደረገች ነው - ቡና ላኪ
በቻይና ውስጥ በተለይም በወጣቱ ትውልድ ዘንድ የቡና ተጠቃሚዎች ቁጥር እየጨመረ መመጣቱ ለኢትዮጵያ የቻይና ገበያ እድገት አስተዋጻኦ ማድረጉን በቡና የውጭ ንግድ ላይ የተሰማሩት አቤል አየለ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
“... በዚህም ምክንያት የቡና መሸጫ ሱቆች በቻይና ግዛቶች ሁሉ በየቀኑ ማለት ይቻላል በፍጥነት እየተስፋፉ ነው። ይህም ለኢትዮጵያ ቡና ከፍተኛ ፍላጎት ፈጥሯል፣ ይህም የወጪ ንግዳችንን መጠን እንድንጨምር ረድቶናል።”
አቤል አየለ ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር ያላት ከቀረጥ ነፃ የንግድ ስምምነት የቡና የወጪ ንግዱ ለማደጉ በተጨማሪ ምክንያትነት ጠቅሰዋል፡፡
“አውሮፓ እና አሜሪካ ከአፍሪካ አገራት በሚመጡ ዕቃዎች ላይ ከፍተኛ ቀረጥ እየጣሉ ነው። ቻይና ግን በተቃራኒው የተለያዩ ቀረጦችን እንዲሁም የገቢ ንግድ እገዳዎችን እያነሳች በመሆኑ፣ በቻይናና በኢትዮጵያ መካከል የንግድ ትስስር እንድናደርግ የበለጠ ምቹ እየሆነልን ነው።”
የምዕራባውያን አገራት ከአፍሪካ አገራት ጋር ንግድ ሲሰሩ የራሳቸው አጀንዳዎች አሏቸው ያሉት የቡና ላኪው፣ ከዚህ አንጻር የኢትዮጵያ የብሪክስ ተሳትፎ አዳዲስ ዕድሎችን ሊያመጣ እንደሚችል ጠቁመዋል።
“ብሪክስ በምዕራባውያን የሚመራውን የንግድ መሰናክል ለመቀነስ ይረዳል። ለምሳሌ በክፍያ ረገድ በዶላር ፋንታ በሀገር ውስጥ ገንዘብ የንግድ ልውውጥ ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት ቢኖር ትልቅ እገዛ ይኖረዋል’’ ሲሉ አሰራሩ ከተመቻቸ ለሀገር እድገትና ለህዝብ ተጠቃሚነት ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል ብለዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X