ትራምፕ የጋዛ የሰላም ዕቅድ ሁለተኛ ምዕራፍ መጀመሩን ይፋ አደረጉ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱትራምፕ የጋዛ የሰላም ዕቅድ ሁለተኛ ምዕራፍ መጀመሩን ይፋ አደረጉ
ትራምፕ የጋዛ የሰላም ዕቅድ ሁለተኛ ምዕራፍ መጀመሩን ይፋ አደረጉ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 16.01.2026
ሰብስክራይብ

ትራምፕ የጋዛ የሰላም ዕቅድ ሁለተኛ ምዕራፍ መጀመሩን ይፋ አደረጉ

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ ያወጡትን መግለጫ ተከትሎ፤ ዩናይትድ ስቴትስ የጋዛን ግጭት ለመፍታት ያዘጋጀችው ባለ 20 ነጥብ ዕቅድ "በይፋ ወደ ቀጣዩ ምዕራፍ ተሸጋግሯል" ብለዋል።

ሁለተኛው ምዕራፍ ከተኩስ አቁም ወደ ትጥቅ መፍታት፣ በባለሙያዎች ወደሚመራ አስተዳደር እና ወደ መልሶ ግንባታ እንደሚሸጋገር እንዲሁም እሳቸው በሚመሩት ዓለም አቀፍ "የሰላም ቦርድ" ስር የሽግግር ወቅት "የጋዛ አስተዳደር ብሔራዊ ኮሚቴ" የተሰኘ የፍልስጤም የባለሙያዎች አስተዳደር ምስረታን እንደሚያካትት ተናግረዋል።

"የሰላም ቦርዱ ሰብሳቢ እንደመሆኔ፤ በቦርዱ ከፍተኛ ተወካይ በመታገዝ በሽግግር ወቅት ጋዛን የሚያስተዳድረውን አዲሱን የፍልስጤም የባለሙያዎች መንግሥት፤ የጋዛ አስተዳደር ብሔራዊ ኮሚቴን፤ እደግፋለሁ" ብለዋል።

በሁለተኛው ምዕራፍ በግብፅ፣ ቱርክ እና ኳታር ድጋፍ የጦር መሳሪያዎችን ማስረከብ እና ዋሻዎችን ማፍረስ ጨምሮ ሃማስ ሙሉ በሙሉ ትጥቅ እንዲፈታ እንደሚደርግ ትራምፕ አመልክተዋል፡፡

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0