ኢትዮጵያ በጅቡቲ በኩል የነዳጅ እና የማዳበሪያ ምርቶችን ወደ ውጭ በመላክ ቀጠናዊ ንግድን ልታሳድግ መሆኑን የጅቡቲው ባለሥልጣን ገለፁ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ በጅቡቲ በኩል የነዳጅ እና የማዳበሪያ ምርቶችን ወደ ውጭ በመላክ ቀጠናዊ ንግድን ልታሳድግ መሆኑን የጅቡቲው ባለሥልጣን ገለፁ
ኢትዮጵያ በጅቡቲ በኩል የነዳጅ እና የማዳበሪያ ምርቶችን ወደ ውጭ በመላክ ቀጠናዊ ንግድን ልታሳድግ መሆኑን የጅቡቲው ባለሥልጣን ገለፁ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 15.01.2026
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ በጅቡቲ በኩል የነዳጅ እና የማዳበሪያ ምርቶችን ወደ ውጭ በመላክ ቀጠናዊ ንግድን ልታሳድግ መሆኑን የጅቡቲው ባለሥልጣን ገለፁ

ይህ እንቅስቃሴ ሀገሪቱ የውጭ ምርቶችን ከማስገባት ይልቅ ወደ ውጭ በመላክ ላይ ወደተመሰረተ የምጣኔ ሀብት ሞዴል ለማሸጋገር ያላትን ስትራቴጂያዊ እቅድ የሚያንፀባርቅ ነው ሲሉ የጅቡቲ ወደቦችና ነፃ የንግድ ቀጣና ባለሥልጣን ኃላፊ አብዲቃድር ኡመር ሀዲ ለጂቡቲ ሚዲያ በሰጡት ቃለ መጠይቅ አሳውቀዋል፡፡

"ኢትዮጵያ ከውጭ የምታስገባውን በመቀነስ የምትልከውን ለመጨመር ትሻለች፡፡ አንድ ሀገር ከፍጆታዋ በላይ ስታመርት ኢኮኖሚዋ እየጠነከረ ይሄዳል" በማለት ጅቡቲ ለውጡን ለመደገፍ ዝግጁ መሆኗን አብዲቃድር ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት 1.8 ሚሊየን ቶን የግብርና ማዳበሪያ ታስገባለች ያሉት ባለሥልጣኑ፣ አሁን ግን የነዳጅ ምርቶችን እና የግብርና ግብዓቶችን ወደ ውጭ ለመላክ አቅዳለች፤ ጅቡቲም ቀዳሚ የሎጂስቲክስ መተላለፊያ ሆና ታገለግላታለች ብለዋል።

ከሰሞኑ ወደ ጅቡቲ የሥራ ጉብኝት ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዶራሌህ ሁለገብ ወደብ እና የሆራይዘን ነዳጅ ተርሚናልን ጎብኝተዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0