የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት፣ ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር የተላከ ልዩ መልዕክት ተቀበሉ
11:18 15.01.2026 (የተሻሻለ: 11:24 15.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት፣ ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር የተላከ ልዩ መልዕክት ተቀበሉ
ሳልቫ ኪር ማያርዲት በትናትናው ዕለት፣ ከኢትዮጵያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ የዐቢይ አሕመድም መልክዕክት መቀበላቸውን የፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት አስታውቋል። በዚህ ወቅት ሁለቱ ወገኖች በሀገራቱ መካከል ያለውን ጥልቅ አጋርነት የሚያጎላ ውይይት አድርገዋል።
በኢትዮጵያው መሪ የተላከው ልዩ መልዕክት፣ በሁለትዮሽ ግንኙነት፣ እንዲሁም በቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑን የደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሞንዴ ሰማያ ኩምባ ገልጸዋል ሲል ጽሕፈት ቤቱ አስታውቋል።
የኢትዮጵያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ የጁባ እና የአዲስ አበባ ግንኙነት ለበርካታ አስርት ዓመታት የዘለቀ፣ በጋራ ትግል እና መስዋዕትነት ላይ የተመሠረተ እንዲሁም ለቀጣናው መረጋጋት ወሳኝ መሆኑንም ጠቁመዋል።
አክለውም፤ ውይይቱ ኢኮኖሚያዊ ትብብርን ማሻሻል ላይ ያተኮረ እንደነበር ጠቁመው፣ ሁለቱም ወገኖች በንግድ እና በልማት ፕሮጀክቶች የጋራ ተጠቃሚነትን ለማስፋፋት ያላቸውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል ሲል የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።
በዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ የተመራው ልዑክ የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ሀብታሙ ኢተፋን ጨምሮ ሌሎች ባለሥልጣናትን ያካተተ ነበር፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

