‘አሁንም መሠረታዊ አለመግባባት አለን’ - የዴንማርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

ሰብስክራይብ

‘አሁንም መሠረታዊ አለመግባባት አለን’ - የዴንማርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

​“ለእኛ፣ የዴንማርክ መንግሥትን የግዛት አንድነት እና የግሪንላንድ ህዝብ የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብትን የማያከብሩ ሃሳቦች በእርግጠኝነት ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት የሌላቸው ናቸው” ሲሉ  ላርስ ራስሙሰን፣ ከምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ እና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ጋር በዋሽንግተን ከተገናኙ በኋላ ተናግረዋል።

​ራስሙሰን እንደገለጹት፣ ሁሉቱም ወገኖች የግሪንላንድ የረጅም ጊዜ ደህንነት አስመልከቶ “ግልጽ ግን ደሞ ገንቢ” ውይይት አድርገዋል። ሆኖም ዴንማርክ የሀገሪቱ ደህንነት አሁን ባለው ማዕቀፍና እ.ኤ.አ.በ1951 የዴንማርክ የመከላከያ ስምምነት እና የኔቶ  ውልን በማካተት ሊረጋገጥ ይችላል ብላ እንደምታምን አክለዋል።

​ዴንማርክ እና አሜሪካ፣ የዴንማርክንቀይ መስመሮች” በማክበር የአሜሪካን የደህንነት ስጋቶች ለመፍታት ከፍተኛ የሥራ ቡድን ለማቋቋም መስማማታቸውን የገለጹ ሲሆን፣ የመጀመሪያው ስብሰባም “በጥቂት ሳምንታት ውስጥ” እንደሚካሄድ ይጠበቃል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0