የኡጋንዳ አጠቃላይ ምርጫ - ቁልፍ ክንውኖች አጠቃላይ ሁኔታዎች

ሰብስክራይብ

የኡጋንዳ አጠቃላይ ምርጫ - ቁልፍ ክንውኖች አጠቃላይ ሁኔታዎች

​እንደ መገናኛ ብዙኃን ዘገባዎች ከሆነ የምርጫው አጠቃላይ ሁኔታው የሚከተለውን ይመስላል፦

🟠 ኡጋንዳ ከፍተኛ የደህነት ጥበቃ ባለበት እና በመላ አገሪቱ የኢንተርኔት አገልግሎት በተቋረጠበት ሁኔታ በነገው ዕለት አጠቃላይ ምርጫ ታካሂዳለች።  ከምርጫዉ በፊት የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲቋረጥ የተደረገው የሕዝብን ደህንነት እና የአገርን ሰላም ለመጠበቅ ታስቦ እንደሆነ ባልስልጣናቱ ገልጸዋል።

🟠 ማህበራዊ የትስስር ገፆች እና የመልእክት መላላኪያ መተግበሪያዎችን ጨምሮ የኢንተርኔት አገልግሎቶች ታግደዋል፤ ሆኖም የድምፅ ጥሪ እና የፅሁፍ መልእክት (ኤስኤምስ) አሁንም እየሠሩ ናቸው። አገልግሎቱ መቼ እንደሚመለስ የተቀመጠ የጊዜ ሰሌዳ የለም።

​🟠 በመላ አገሪቱ ከፍተኛ የደህንነት ኃይሎች ተሰማርተዋል። ባለሥልጣናት ይህ ስምሪት ሥርዓትን ለማስከበር እንደሆነ ተናግረዋል።

🟠 የምርጫ ኮሚሽኑ በበኩሉ የምርጫ ቁሳቁሶች በመላ አገሪቱ መሰራጨታቸውን እና በአብዛኛው ዝግጁ መሆኑን ገልጿል። የድምፅ አሰጣጥ ስርዓቱ ከጠዋቱ 1 ሰዓት እስከ አመሻሽ 10 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ በጥብቅ መመሪያዎች ስር እንደሚከናወን ታቅዷል።

🟠 በፕሬዝዳንታዊ ውድድሩ በወቅቱ ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ እና በዋናው ተቃዋሚ መሪ ሮበርት ኪያጉላኒ (ቦቢ ዋይን) የሚመሩ 8 እጩዎች ይሳተፋሉ።

​🟠 በምርጫው ለመሳተፍ 21.6 ሚሊዮን የሚጠጉ መራጮች ተመዝግበዋል። የምርጫው ውጤት ድምፅ አሰጣጡ ከተጠናቀቀ ከ48 ሰዓታት በኋላ ይፋ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

🟠 የምሥራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ  ምርጫውን እንዲታዘቡ 61 ታዛቢዎችን አሰማርቷል።

ከማኅበራዊ ሚዲያ የተገኙ ቪዲዮዎች

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0