#viral | የአይሾውስፒድ የኢትዮጵያ ቆይታ - ቀጥታ ሥርጭት ላይ ያጋጠመው የሆድ መታወክ መነጋግሪያ ሆኗል

ሰብስክራይብ

#viral | የአይሾውስፒድ የኢትዮጵያ ቆይታ - ቀጥታ ሥርጭት ላይ ያጋጠመው የሆድ መታወክ መነጋግሪያ ሆኗል

አይሾውስፒድ በመባል በቅጽል ሰሙ የሚያታወቀው ዝነኛው የዩቲብ የቀጥታ ዝግጀት አስተላላፊ (ስትሪመር) ዳረን ጄሰን ዋትኪንስ ጁኒየር፣ በኢትዮጵያ የነበረው ቆይታ በተለያዩ እንቅስቃሴዎች የታጀበ የ5 ሰዓታት የቀጥታ ስርጭት እስካሁን ደረስ ከ10.1 ሚሊዮን በላይ እይታ አግኝቷል።

ዩቲዩበሩ እንጀራ እና ቡናን ጨምሮ የሀገር ውስጥ ምግቦችን የቀመሰ ሲሆን፣ ጥሬ ስጋ በመሞከር ከተለመደው የአመጋገብ ዘይቤው ወጣ ያለ ሙከራ ማደርጉ ምቾት እንደነሳው ለተከታዮቹ በግልፅ በመንገር ለተወሰኑ ደቂቃዎቸ ከቀጥታ ስርጭቱ ራሱን አግልሏል፡፡

ስፒድ በቀጥታ ሥርጭቱ ወቅት ያጋጠመው የሆድ መታወክ ከኢትዮጵያ ውጭ ያሉ የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ከቀመሰው ጥሬ ሥጋ በማያያዝ የተለያዩ አስቂኝ አስተያየቶች ሲሰጡ ተስተውለዋል፡፡

በኢትዮጵያ የበነበረው ቆይታ እጅግ ደስተኛ መሆኑን እና በሺዎች የሚቆጠሩ አድናቂዎቹን ማግኘት እንደቻለ አስታውቋል፡፡ ከ283 ሺህ በላይ ተመልካቾች የቀጥታ ስርጭቱን ተከታትለዋል፤ ከ280 ሺህ በላይ አዳዲስ የዩቲዩብ ተመዝጋቢዎችን (ሰብስክራይበሮችን) አፍርቷል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0