ኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር ለመፎካከር የጆሞ ኬንያታ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግዙፍ የማስፋፊያ ዕቅድ ይፋ ማድረጓ ተዘገበ
19:38 14.01.2026 (የተሻሻለ: 19:44 14.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር ለመፎካከር የጆሞ ኬንያታ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግዙፍ የማስፋፊያ ዕቅድ ይፋ ማድረጓ ተዘገበ
የማስፋፊያ ስራው ለረጅም ጊዜ ከዘገየ በኋላ ቀጣናዊ ተፎካካሪዎች በአዲስ የአውሮፕላን ማረፊያ መሰረተ ልማት ወደፊት እየገሰገሱ በመሆኑ ሀገሪቱ ገንባታውን ፍጥነት ለመጀመር ቁርጠኝነቷን በድጋሚ አረጋግጣለች ሲሉ የትራንስፖርት ካቢኔ ፀሐፊ ዴቪስ ቺርቺር ገልፀዋል፡፡
ኢትዮጵያ ያሰጀመረችው ግዙፍ አዲስ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እና ሩዋንዳ በኳታር ድጋፍ የቡገሴራ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያን እየገነባች መሆኑን በመጥቀስ የኬንያ ሚዲያ ዘግቧል፡፡
የ ዕቅዱ ዋና አካል በኤክስ ቅርጽ የሚገነባ እስከ 15 ሚሊዮን መንገድኞችን የሚያስተላልፍ አዲስ የመንገደኞች ተርሚናል ያካተተ ሲሆን፣ የአውሮፕላን ማኮብኮቢያ፣ ሆቴሎች፣ የሎጂስቲክስ ፓርኮችን እና የንግድ ወረዳዎችን የያዘ "የአውሮፕላን ማረፊያ ከተማ" መገንባትም በዕቅዱ ውስጥ ተካተዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X