ሦስተኛው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ በጎርጎሮሳዊያኑ 2026 እንዲካሄድ ታቅዷል - ላቭሮቭ
18:13 14.01.2026 (የተሻሻለ: 18:14 14.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሦስተኛው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ በጎርጎሮሳዊያኑ 2026 እንዲካሄድ ታቅዷል - ላቭሮቭ
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ሞስኮ ውስጥ ከናሚቢያ አቻቸው ሴልማ አሺፓላ-ሙሳቪ ጋር ባደረጉት ውይይት ስለሚመጣው ጉባኤ መምከራቸውን ተናግረዋል።
እ.ኤ.አ. በ2019 የተመሠረተው የሩሲያ-አፍሪካ አጋርነት ፎረም ቀደም ሲል ሁለት ጉባኤዎችን አስተናግዷል። በ2019 በሩሲያዋ ሶቺ እና በ2023 በሴንት ፒተርስበርግ የተካሄዱ ሲሆን፣ የመጀመሪያው የሚኒስትሮች ጉባዔ በጎርጎሮሳዊያኑ አቆጣጠር ህዳር 2024 ተካሂዷል።
የሁለተኛው የሚኒስትሮች ጉባዔ ባለፈው ታህሳስ ካይሮ ውስጥ የተካሄደ ሲሆን፣ ይህም ዝግጅቱ በአፍሪካ ምድር ላይ ሲካሄድ የመጀመሪያው ነበር። ጉባኤው የ52 የአፍሪካ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተወካዮችን በማሳተፍ የአጋርነት ፎረሙ የቅርብ ጊዜው ከፍተኛ ደረጃ ስብሰባ ሆኖ ተመዝግቧል።
የካይሮው ስብሰባ የተጠናቀቀው በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ የጋራ አቋምን የሚያንጸባርቅ እና ከሚቀጥለው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ በፊት ትብብርን ለማጠናከር ቃል የሚገባ የጋራ መግለጫ በማውጣት ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X