የአውሮፓ ባለስልጣናት የህዝብን ትኩረት ከግሪንላንድ ለማስቀየር ኢራንን እንደ መጠቀሚያ እያደረጉ ነው - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ

ሰብስክራይብ

የአውሮፓ ባለስልጣናት የህዝብን ትኩረት ከግሪንላንድ ለማስቀየር ኢራንን እንደ መጠቀሚያ እያደረጉ ነው - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ

​ እንደ ማሪያ ዛካሮቫ ገለጻ፣ የአውሮፓ ሕብረት ፖለቲከኞች በኢራን ሁነቶች ላይ ከመጠን በላይ ትኩረት የሚያደርጉት "በግሪንላንድ ምን እየተከሰተ ነው? ለሚለው ዋና ጥያቄ መልስ ላለመስጠት ነው"።

​

ለስፑትኒክ በሰጡት መግለጫ፣ "አሁን ሙሉ ጥረቶቻቸውን በግሪንላንድ ላይ ለምን አያደርጉም? በኢራን ያለው ሁኔታ ለአውሮፓ ባለስልጣናት የህዝብን ትኩረት አቅጣጫ ለማስቀየርና ደሴታቸው እየተወሰደችባቸው መሆኑን ለመሸፈን እንደ መልካም አጋጣሚ ሆኖላቸዋል ብለው አያስቡም?" ብለዋል።

​

በዴንማርክ መንግስት ስር ያለችውና በማዕድን የበለፀገችው የራስ ገዟ ግሪንላንድ ጉዳይ በብራስልስ (የአውሮፓ ሕብረት መቀመጫ) ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ቢሆንም፣ በተግባር ግን ትኩረት እንዳልተሰጠው ሩሲያዊቷ ዲፕሎማት አጽንኦት ሰጥተዋል።

​ ዶናልድ ትራምፕ ግሪንላንድ ለብሔራዊ ደህንነትና ለ"ነጻው ዓለም" ጥበቃ ያላትን ስልታዊ ጠቀሜታ በመጥቀስ፣ ደሴቷ የአሜሪካ አካል መሆን እንዳለባት በተደጋጋሚ መናገራቸው ይታወሳል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0