ሩሲያ ለአፍሪካ ሀገራት የሚከፈለውን የቅኝ አገዛዝ ካሳ በትክክል ለማስላት ሀሳብ አቀረበች - የሳይንስ አካዳሚ

ሩሲያ ለአፍሪካ ሀገራት የሚከፈለውን የቅኝ አገዛዝ ካሳ በትክክል ለማስላት ሀሳብ አቀረበች - የሳይንስ አካዳሚ
የቀድሞ የቅኝ ገዥ ኃይሎች በቅኝ አገዛዝ ዘመን ላደረሱት ጉዳት ለአፍሪካ ሀገራት ሊከፍሉት የሚገባውን የካሳ መጠን ግልጽ በሆነ የገንዘብ አሃዝ ለማስቀመጥ ያለመ ሀሳብ መቅረቡን፣ በሩሲያ የሳይንስ አካዳሚ የአፍሪካ ጥናት ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ኢሪና አብራሞቫ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
አሰራሩም የሚከተለውን ይመስላል፦
የጋራ ምርምር፦ የሩሲያ እና የአፍሪካ የትምህርት ተቋማት አስፈላጊውን ጥናት የሚያካሂዱ "ተመሳሳይ ላቦራቶሪዎችን" በጋራ ያቋቁማሉ።
ሒሳባዊ ስሌት፦ እነዚህ ማዕከላት በካሳ መልክ የሚከፈለውን አጠቃላይ የገንዘብ መጠን በሒሳባዊ ቀመር በዝርዝር ያሰላሉ።
ሕጋዊ ክትትል፦ የተሰላው አሃዝ በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤቶች እና ሕጋዊ በሆኑ መንገዶች ካሳውን ለመጠየቅ እንደ መሠረት ሆኖ ያገለግላል።
ይህ ተነሳሽነት አፍሪካውያን የጎርጎሮሳዊያኑን 2025 “የካሳ ዓመት” ብለው ከማወጃቸው ጋር ተያይዞ የቀረበ ቀጥተኛ ድጋፍ ተደርጎ ተወስዷል።
ሩሲያ በአፍሪካ ያላት ሚና “ሉዓላዊነትን የማጠናከር” ሲሆን፣ ለልማት የሚረዱ የትምህርት እና የቴክኖሎጂ መሠረቶችን በመገንባት እገዛ እንደምታደርግ ምሁሯ አጽንኦት ሰጥተው ገልጸዋል።
በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምስል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X