የአደይ አበባ ስቴዲየም ዋናው የመጫወቻ ሜዳ በ86% ውጤት የፊፋን እውቅና አገኘ
14:49 14.01.2026 (የተሻሻለ: 14:54 14.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የአደይ አበባ ስቴዲየም ዋናው የመጫወቻ ሜዳ በ86% ውጤት የፊፋን እውቅና አገኘ
አዲሱ አደይ አበባ ኢንተርናሽናል ስቴዲየም ሜዳ በዓለም አቀፉ የእግርኳስ ማሕበር (ፊፋ) እውቅና ያለውን የፈተና ተቋም ላቦስፖርት (LABOSPORT) ጥብቅ ግምገማ አልፎ የፊፋን ማረጋገጫ አግኝቷል።
የስቴዲየሙ ዋና ሜዳ በፊፋ የተፈጥሮ የመጫወቻ ሜዳዎች ደረጃ ልኬት አስደናቂ የ86 በመቶ ውጤት አስመዝግቧል፡፡ ይህም ከፍተኛ ምድብ ውስጥ አስቀምጦታል፡፡ ገምጋሚው አካል “ዉሱንነት የሌለበት እጅግ በጣም ጥሩ።” በሚል አስቀምጦታል፡፡
ግምገማው ሜዳው ለዋና ዋና ውድድሮች ዝግጁ መሆኑን አሳይቷል። እንደ ስቴዲየሙ ታሪክ፣ ግንባታ፣ የሳር ዝርያ ሽግግር እና ወቅታዊ ለውጥ ያሉ ቁልፍ ነገሮች ዝቅተኛ ስጋት ተብለዋል፡፡
ይህ ደረጃ ሜዳው ለደህንነት፣ ለጨዋታ እና ለመጫወቻነት ዓለም አቀፍ መስፈርቶችን ማሟላቱን ያረጋግጣል። እውቅናው ለኢትዮጵያ የስፖርት መሠረተ ልማት ትልቅ ምዕራፍ ነው፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia
/