ዳቺ የምግብ ኢንዲስትሪ ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ የተቀነባበሩ የጥራጥሬ ምርቶችን ለገበያ አቀረበ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱዳቺ የምግብ ኢንዲስትሪ ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ የተቀነባበሩ የጥራጥሬ ምርቶችን ለገበያ አቀረበ
ዳቺ የምግብ ኢንዲስትሪ ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ የተቀነባበሩ የጥራጥሬ ምርቶችን ለገበያ አቀረበ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 14.01.2026
ሰብስክራይብ

ዳቺ የምግብ ኢንዲስትሪ ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ የተቀነባበሩ የጥራጥሬ ምርቶችን ለገበያ አቀረበ

ምርቱ ሀገሪቱ ከውጭ በሚገቡ የተቀነባበሩ ምግቦች ላይ ያላትን ጥገኝነት ለመቀነስና እሴት የተጨመረባቸው የወጪ ንግድ ምርቶችን ለማስፋፋት ለምታደርገው ጥረት ትልቅ ምዕራፍ መሆኑ ተገልጿል።

የተቀነባበሩት ምርቶችም ቀይ ቦሎቄ፣ ጥቁር ቦሎቄ፣ ነጭ ቦሎቄ፣ ባቄላ፣ ሽምብራ እና ጣፋጭ በቆሎ ሲሆኑ በ400 ግራም የቀርቡትን ምርቶቸ በሚቀጥሉት ሁለት ወራት በሦስት ኪሎ ግራም መጠኖች ወደ ገበያ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

“በኢትዮጵያ የተመረተ” በሚል መለያ ለሀገር ውስጥ እና እንደ ዱባይ ላሉ  የውጭ ሀገር መዳረሻዎች የታሰቡት ምርቶቸ ሙሉ የጥሬ ዕቃ ግብዓታቸው፣ ከአነስተኛ አምራቾች እና የንግድ አርሶ አደሮች የተገኙ መሆናቸውን የኩባንያው ኃላፊዎች ገልጸዋል።

ፕሮጀክቱ የውጭ ንግድ ገቢን ለማሳደግ፣ በማምረቻ እና በሎጂስቲክስ ዘርፎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር እና ለአርሶ አደሮች የተረጋጋ የገቢ ምንጭ እንዲኖር አስተዋጽኦ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል ሲል የአገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0