የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሳዑዲ አረቢያዋ ጂዛን አዲስ የበረራ መስመር ጀመረ
12:50 14.01.2026 (የተሻሻለ: 12:54 14.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሳዑዲ አረቢያዋ ጂዛን አዲስ የበረራ መስመር ጀመረ
አየር መንገዱ በቀጣናዊ ጉዞ ትስስር ላይ ያሰመዘገበው ትልቅ ስኬት የተባለለት ይህ አዲስ መሰመር፣ ለንግድም ሆነ ለመዝናኛ ተጓዦች ሰፋ ያሉ አማራጮችን ለማቅረብ ያለመ ነው፡፡
አዲሱ የበረራ መስመር፣ በኢትዮጵያ እና በሳዑዲ አረቢያ መካከል ያለውን ግንኙነት እንደሚያጠናክርና በሁለቱ አገራት መካከል እያደገ ላለው የቱሪዝም እና የንግድ ዘርፍ ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥር ይጠበቃል።
በሳዑዲ አረቢያ የቀይ ባሕር ዳርቻ ላይ የምትገኘው ጂዛን በባህላዊ ቅርሶቿ፣ ውብ መልክዓ ምድሯ እና ለታሪካዊ ስፍራዎች ባላት ቅርበት የምተትታወቅ ሲሆን፣ የቀጥታ በረራው ለዓለም አቀፍ ቱሪስቶች እና ለነጋዴዎች ጂዛን ለመድረስ ቀላል ያደርግላቸዋል።
ጅዳ ፣ሪያድ፣ ዳማም እና መዲና በቅደም ተከተል የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስቀድሞ በረራ የሚያድርግባቸው የሳዑዲ አረቢያ መደረሻዎች ናቸው፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X