ኦሮሚያ ክልል ከ260 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ 8,300 በላይ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን ማጽደቁ ተዘገበ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኦሮሚያ ክልል ከ260 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ 8,300 በላይ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን ማጽደቁ ተዘገበ
ኦሮሚያ ክልል ከ260 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ 8,300 በላይ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን ማጽደቁ ተዘገበ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 14.01.2026
ሰብስክራይብ

ኦሮሚያ ክልል ከ260 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ 8,300 በላይ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን ማጽደቁ ተዘገበ

የኦሮሚያ ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት፣ የክልሉ ኢንቨስትመንት ቦርድ በሁለት ዙር ባስተላለፈው ውሳኔ ለፕሮጀክቶቹ ፈቃድ መስጠቱ ተገልጿል።

በመጀመሪያው ዙር ከ90 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ 3,163 ፕሮጀክቶች፤ በሁለተኛው ዙር ደግሞ ከ172 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያላቸው 5,158 ፕሮጀክቶች መጽደቃቸውን የቢሮ ኃላፊውን ጠቅሶ የአገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።

የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶቹ፦

በአጠቃላይ 143 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የሚያርፉ ናቸው፡፡

ከ691 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥሩ ይጠበቃል፡፡

ለክልሉ መንግሥት ከ51 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ እንደሚያስገኙ ተነግሯል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0