ሩሲያ እና ናሚቢያ በዊንድሆክ ለሚካሄዱ የከፍተኛ ደረጃ ውይይቶች እየተዘጋጁ ነው
ሩሲያ እና ናሚቢያ በዊንድሆክ ለሚካሄዱ የከፍተኛ ደረጃ ውይይቶች እየተዘጋጁ ነው
ሞስኮ እና ዊንድሆክ በጎርጎሮሳዊያኑ 2026 በናሚቢያ ለሚካሄደው 11ኛው የሩሲያ-ናሚቢያ በይነ-መንግሥታት የንግድ እና ኢኮኖሚ ትብብር ኮሚሽን ስብሰባ የመጨረሻ ዝግጅቶችን እያጠናቀቁ ነው።
ውሳኔው የተረጋገጠው የኮሚሽኑ ሊቀ-መናብርት በሆኑት የሩሲያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ዩሪ ትሩትኔቭ እና የናሚቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሴልማ አሺፓላ-ሙሳቪ መካከል በሞስኮ ባደረጉት ስብሰባ ላይ መሆኑን ትሩትኔቭ የፕሬስ አገልግሎት አስታውቋል፡፡
ትሩትኔቭ በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን “ዘላቂ ወዳጅነት” አበክረው የገለጹ ሲሆን፣ የናሚቢያ ፕሬዝዳንት ናንዲ-ንዳይትዋ ወደ ሩሲያ በተደጋጋሚ ያደረጉትን ጉብኝት እና ለሞስኮ ያላቸውን ቀጣይነት ያለው በጎ አመለካከት አስታውሰዋል። አክለውም፣ አሺፓላ-ሙሳቪ ለፕሬዝዳንቷ የግል ምስጋናቸውን እና መልካም ምኞታቸውን እንዲያደርሱላቸው ጠይቀዋል።
ሁለቱ ወገኖች የንግድ ልውውጥን ማሳደግ፣ በጂኦሎጂ እና በማዕድን ቁፋሮ፣ በትምህርት ዘርፍ ስላለው ትብብር የተወያዩ ሲሆን፤ በ2026 ከሚካሄደው የኮሚሽኑ ስብሰባ ጎን ለጎን በሩሲያ ድጋፍ የሚደረግ የንግድ ፎረም ለማካሄድ ተስማምተዋል።
አሺፓላ-ሙሳቪ በዛሬው ዕለት ረፈድ ብሎ ከሰርጌ ላቭሮቭ ጋር ውይይት የሚያደርጉ ሲሆን፣ በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫም እንደሚሰጡ ይጠበቃል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X