አሜሪካ ኢራን ውስጥ ጥቃት ሊሰነዘርባቸው በሚችሉ ኢላማዎች ላይ ከአውሮፓ የደህንነት ተቋማት መረጃ መጠየቋ ተዘገበ
11:02 14.01.2026 (የተሻሻለ: 11:04 14.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
አሜሪካ ኢራን ውስጥ ጥቃት ሊሰነዘርባቸው በሚችሉ ኢላማዎች ላይ ከአውሮፓ የደህንነት ተቋማት መረጃ መጠየቋ ተዘገበ
ትራምፕ የኢራንን የኒውክሌር ተቋማት የመምታት እቅድ እንዳላቸው የሚያሳይ ምልክት ባይኖርም፣ ዋሽንግተን በቅርቡ በተቀሰቀሰው ተቃውሞ ወቅት ለተከሰቱ ግጭቶች ተጠያቂ ናቸው ብላ የምታምናቸውን ግለሰቦች ኢላማ የማድረግ እድሏ ከፍተኛ መሆኑን አንድ የአሜሪካ ጋዜጣ የአውሮፓ ባለሥልጣናትን ጠቅሶ ዘግቧል።
ሌላ የአሜሪካ ጋዜጣ የባሕረ ሰላጤው ሀገራትን ምንጮች ጠቅሶ ባወጣው የተለየ ዘገባ፤ ዋሽንግተን በኢራን ላይ ጥቃት ልትፈፅም የምትችልበት "የበለጠ ዕድል" አለ ብሎ እንደሚያምን ገልጿል።
በኢራን የገንዘብ ዋጋ መውደቁን ተከትሎ ባለፈው ታህሳስ መጨረሻ ላይ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፖሊስ ጋር ወደሚደረግ ግጭትና ሁከት በመቀየር ወደ በርካታ ከተሞች ተሰራጭቷል። በዚህም ሳቢያ ከደህንነት ኃይሎችም ሆነ ከተቃዋሚዎች ወገን የሰዎች ሕይወት አልፏል።
ቴህራን ለተከሰተው ሁከት አሜሪካንና እስራኤልን ተጠያቂ ያደረገች ሲሆን፣ ከሁለት ቀናት በፊት ሁኔታው ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር መዋሉን አስታውቃለች።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X