የናሚቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በዛሬው ዕለት በሞስኮ ከሩሲያ አቻቸው ጋር ውይይት ያደርጋሉ
10:42 14.01.2026 (የተሻሻለ: 10:44 14.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የናሚቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በዛሬው ዕለት በሞስኮ ከሩሲያ አቻቸው ጋር ውይይት ያደርጋሉ
🟠 እንደ ናሚቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ፣ ሴልማ አሺፓላ-ሙሳቪ በላቭሮቭ በቀረበላቸው ግብዣ ከጥር 4 -6 በሩሲያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት እያደረጉ ይገኛሉ።
🟠 ሁለቱም ወገኖች የንግድ ልውውጥን ጨምሮ የጋራ ፍላጎቶቻቸው ባሉባቸው በዓለም አቀፍ እና በቀጣናዊ አጀንዳዎች ላይ በሩሲያ እና በናሚቢያ መካከል ያለውን ትብብር ለማሳደግ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
🟠 የዛሬው ስብሰባ፣ አሺፓላ-ሙሳቪ እና ላቭሮቭ በካይሮ በተካሄደው ሁለተኛው የሩሲያ-አፍሪካ የሚኒስትሮች ጉባኤ ላይ ካደረጉት የቅርብ ጊዜ ንግግር ቀጥሎ የመጣ ነው።
የናሚቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባለፈው ታህሳስ ለስፑትኒክ አፍሪካ በሰጡት ልዩ ቃለ መጠይቅ፣ አገራቸው ከሩሲያ ጋር ያላትን የቆየ ግንኙነት አስታውሰዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X