ናይጄሪያ ውስጥ ከሽፈው የተገኙ ሚሳኤሎች በአሜሪካ ዝና እና በእውነተኛ ወታደራዊ አቅሟ መካከል ያለውን ሰፊ ልዩነት ያሳያሉ - ናይጄሪያዊዉ ፕሮፌሰር

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱናይጄሪያ ውስጥ ከሽፈው የተገኙ ሚሳኤሎች በአሜሪካ ዝና እና በእውነተኛ ወታደራዊ አቅሟ መካከል ያለውን ሰፊ ልዩነት ያሳያሉ - ናይጄሪያዊዉ ፕሮፌሰር
ናይጄሪያ ውስጥ ከሽፈው የተገኙ ሚሳኤሎች በአሜሪካ ዝና እና በእውነተኛ ወታደራዊ አቅሟ መካከል ያለውን ሰፊ ልዩነት ያሳያሉ - ናይጄሪያዊዉ ፕሮፌሰር - Sputnik አፍሪካ, 1920, 13.01.2026
ሰብስክራይብ

ናይጄሪያ ውስጥ ከሽፈው የተገኙ ሚሳኤሎች በአሜሪካ ዝና እና በእውነተኛ ወታደራዊ አቅሟ መካከል ያለውን ሰፊ ልዩነት ያሳያሉ - ናይጄሪያዊዉ ፕሮፌሰር

​በናይጄሪያ ውስጥ የተጣሉት የአሜሪካ የክሩዝ ሚሳኤሎች አለመፈንዳት፤ በመረጃ አሰባሰብ፣ በዕቅድ እና በአፈፃፀም ላይ ያሉ ጉልህ ድክመቶችን ያሳያል ሲሉ በአቡጃ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ኢኮኖሚ እና የልማት ጥናት ፕሮፌሰር አቡበከር ሳዲቅ አባ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

​የአሜሪካ ወታደራዊ ቴክኖሎጂ ከዓለም አቀፋዊ ተጨባጭ ሁኔታዎች ጋር የማይጣጣም መሆኑን የጠቀሱት ፕሮፌሰሩ፣ ብዙውን ጊዜ እንደ ናይጄሪያ ገጠራማ አካባቢዎች ያሉ የተወሰኑ አካባቢዎችን ግምት ውስጥ ማስገባት ያቅተዋል ብለዋል፡፡

እንደ ባለሙያው ገለፃ፣ ያልፈነዱ የሚሳኤል  ጭንቅላቶች የሚያስከትሏቸው አደጋዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

🟠 ሥነ-ልቦናዊ ተፅእኖ፦ ገበሬዎች ወደ እርሻቸው ለመመለስ በመፍራታቸው ምክንያት የዕለት ተዕለት ኑሮአቸው እና የምግብ ምርት ይስተጓጎላል፡፡

🟠 አካባቢያዊ አደጋ፦ ያልፈነዱ የሚሳኤል ጥይቶች መሬቱን ከመበከላቸውም በላይ የረጅም ጊዜ የደህንነት ስጋት ይፈጥራሉ፡፡

🟠 የደህንነት ስሜት፦ የሚሳኤል ጥቃቱ ናይጄሪያ በባዕድ ወረራ ስር እንደወደቀች እንዲሰማት በማድረግ፣ አገራዊ ስጋትን ከፍ አድርጎታል፡፡

🟠 የአደጋ አለመመጣጠን፦ እነዚህ በሲቪሎች ላይ የሚደርሱ አደጋዎች፣ ዘመቻው በመነሻው ሊፈታው ካሰበው የደህንነት ስጋት እጅግ የላቁ ናቸው።

​ፕሮፌሰር አባ አሜሪካ ለወሰደችው "ግዴለሽነት" የተሞላበት እርምጃ ተጠያቂ እንድትሆን ዓለም አቀፍ ትብብር እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል።

ናይጄሪያ፣ በአገሪቱ ሰሜናዊ ግዛት በእነዚህ ሚሳኤሎች ለደረሰው ጉዳት ካሳ ለመጠየቅ የኢኮኖሚ እና የዲፕሎማሲ መንገዶችን መጠቀም እንዳለባት በማሳሰብ ፕሮፌሰሩ አስተያየታቸውን አጠቃለዋል።

በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለጸገ ምስል

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0