ኢራን በአሜሪካ ተፅዕኖ ምክንያት በደቡብ አፍሪካ ጥያቄ አቅራቢነት ከብሪክስ ፕላስ ልምምድ ራሷን አገለለች - ዘገባዎች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢራን በአሜሪካ ተፅዕኖ ምክንያት በደቡብ አፍሪካ ጥያቄ አቅራቢነት ከብሪክስ ፕላስ ልምምድ ራሷን አገለለች - ዘገባዎች
ኢራን በአሜሪካ ተፅዕኖ ምክንያት በደቡብ አፍሪካ ጥያቄ አቅራቢነት ከብሪክስ ፕላስ ልምምድ ራሷን አገለለች - ዘገባዎች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 13.01.2026
ሰብስክራይብ

ኢራን በአሜሪካ ተፅዕኖ ምክንያት በደቡብ አፍሪካ ጥያቄ አቅራቢነት ከብሪክስ ፕላስ ልምምድ ራሷን አገለለች - ዘገባዎች 

​ከደቡብ አፍሪካ ጋር ከተደረገ ዲፕሎማሲያዊ ንግግር በኋላ፣ ኢራን በደቡብ አፍሪካ የባሕር ዳርቻ በሚካሄደው የብሪክስ ፕላስ የባሕር ኃይል ልምምድ ላይ ያላትን ተሳትፎ ወደ ታዛቢነት ዝቅ ለማድረግ መስማማቷን የደቡብ አፍሪካ መገናኛ ብዙኃን ምንጮችን ጠቅሰው ዘግበዋል።

​ኢራን ሁኔታውን ተገንዝባለች ያሉት በትናንትናው ዕለት የወጡ ዘገባዎች፤ ባለፈው ሳምንት በሲሞን ታውን የባሕር ኃይል ጣቢያ የደረሱ ሁለት የኢራን መርከቦች ባለፈው ማክሰኞ  ማለዳ ከተጀመረው "የሰላም ፍላጎት 2026" ልምምድ ይወጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ አክለዋል።

የደቡብ አፍሪካ ጥያቄ በሚከተሉት ምክንያቶች ላይ የተመሰረተ እንደሆነ ተገልጿል፦

ደቡብ አፍሪካ በስትራቴጂካዊ የባሕር ክልሏ ውስጥ ቻይና የምትመራውን የብሪክስ የባሕር ኃይል ልምምድ እያስተናገደች መሆኗ፣

ፕሪቶሪያ በአሜሪካ ኮንግረስ በሚካሄደው የአፍሪካ ዕድገትና ዕድል ሕግ (አጎአ) ድምፅ አሰጣጥ የንግድ ተመራጭነት የጊዜ ገደብ እንዲራዘምላት ተስፋ ማድረጓ እና

አሜሪካ በኢራን መንግሥት ላይ የያዘችው ጠንካራ አቋም እና በኢራን ውስጥ እየተካሄደ ያለው ተቃውሞ ሁኔታውን ውስብስብ ማድረጉ ናቸው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0