በአይነቱ ልዩ የሆነ የኢትዮጵያ የሕጻናት የደምና ካንሰር ሕክምና ማኅበር በይፋ ተመሠረተ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበአይነቱ ልዩ የሆነ የኢትዮጵያ የሕጻናት የደምና ካንሰር ሕክምና ማኅበር በይፋ ተመሠረተ
በአይነቱ ልዩ የሆነ የኢትዮጵያ የሕጻናት የደምና ካንሰር ሕክምና ማኅበር በይፋ ተመሠረተ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 13.01.2026
ሰብስክራይብ

በአይነቱ ልዩ የሆነ የኢትዮጵያ የሕጻናት የደምና ካንሰር ሕክምና ማኅበር በይፋ ተመሠረተ

ይህ የኢትዮጵያን የጤና ጥበቃ ሥርዓት ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋግራል የተባለው ታሪካዊ እርምጃ፣ በካንሰር እና በደም ሕመሞች ለሚሰቃዩ ሕፃናት የሚሰጠውን እንክብካቤ ለመለወጥ አልሟል።

በምስረታው ላይ የተገኙት የጤና ዴኤታ ሚኒስትር ዶክተር ደረጄ ዱጉማ፣ "የሕፃናት ካንሰርን ለመከላከል የተቀናጀ ግንባር መፍጠር ያስፈልጋል" ያሉ ሲሆን "ማሕበሩ መረጃዎችን ለመሰብሰብ፣ ልዩ የሰለጠኑ ባለሙያዎችን ለማፍራት እና በሽታውን ቀድሞ ለመለየት ወሳኝ ነው። ሚኒስቴሩም የሕፃናት ጠንካራ የጤና መሠረተ ልማት ለመገንባት ከዚህ ማኅበር ጋር በቁርጠኝነት ይሠራል" ሲሉ አፅንዖት ሰጥተዋል።

በኢትዮጵያ በየዓመቱ ከ6 ሺህ እስከ 8 ሺህ የሚሆኑ ሕፃናት በካንሰር በሽታው እንደሚያዙ ቢገመትም፣ ወቅታዊ ሕክምና የሚያገኙት ግን ከ2 ሺህ ያነሱት ብቻ ናቸው። ሚኒስቴሩ የህክምናውን ተደራሽንት ለማሰፋት የአምስት ዓመት መርሃ ግብር ቀርፆ እየሰራ እንደሚገኝ ተመላክቷል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበአይነቱ ልዩ የሆነ የኢትዮጵያ የሕጻናት የደምና ካንሰር ሕክምና ማኅበር በይፋ ተመሠረተ
በአይነቱ ልዩ የሆነ የኢትዮጵያ የሕጻናት የደምና ካንሰር ሕክምና ማኅበር በይፋ ተመሠረተ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 13.01.2026
አዳዲስ ዜናዎች
0