በሞሮኮ ለሰባት ዓመታት የዘለቀው ድርቅ በከባድ የክረምት ዝናብ ምክንያት ማክተሙን የውኃ ሚኒስትሩ ገለጹ

© telegram sputnik_ethiopiaበሞሮኮ ለሰባት ዓመታት የዘለቀው ድርቅ በከባድ የክረምት ዝናብ ምክንያት ማክተሙን የውኃ ሚኒስትሩ ገለጹ
በሞሮኮ ለሰባት ዓመታት የዘለቀው ድርቅ በከባድ የክረምት ዝናብ ምክንያት ማክተሙን የውኃ ሚኒስትሩ ገለጹ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 13.01.2026
ሰብስክራይብ
የክረምቱ የዝናብ መጠን ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር 95 በመቶ፣ ከወቅታዊ አማካኝ መጠን ደግሞ በ17 በመቶ ብልጫ ያለው መሆኑን፤ ይህም የግድቦችን የውኃ ሙሌት መጠን ወደ 46 በመቶ ከፍ ማድረጉንና ዋና ዋና የውኃ ማጠራቀሚያዎች መሙላታቸውን ኒዛር ባራካ ለፓርላማ ተናግረዋል። ይህ ሁኔታ ለዓመታት የውኃ አጠቃቀም ገደብ ተጥሎበት ለነበረው የግብርና ዘርፍ ትልቅ እፎይታን አምጥቷል።
እንደ መገናኛ ብዙኃን ዘገባ ከሆነ ለሰባት ዓመታት የቆየው ድርቅ፦
የሞሮኮን ግድቦች አድርቋል፡፡
የስንዴ ምርትን በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል፡፡
የአገሪቱን የቀንድ ከብቶች ቁጥር በእጅጉ አሳንሷል፡፡
በግብርናው ዘርፍ ከፍተኛ የሥራ ዕድል ቅነሳን አስከትሏል፡፡
ሀገሪቱ የጨው ውኃን ወደ ንጹሕ ውኃ የመቀየር ዕቅዶቿን እንድታፋጥን አድርጓታል።
ሞሮኮ እ.ኤ.አ. እስከ 2030 ድረስ የመጠጥ ውኃ ፍላጎቷን 60 በመቶውን ከባሕር ውኃ ለማግኘት ያለመች ሲሆን  (ይህም ካለበት 25 በመቶ ከፍ ይላል)፤ የግድብ ውኃን ደግሞ ለውስጥ ለውስጥ ክልሎች ለማስቀረት ማቀዷን ባራካ ቀደም ብለው ተናግረዋል።
አዳዲስ ዜናዎች
0