የኢትዮጵያ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ኃላፊ በሞቃዲሾ ድንገተኛ ጉብኝት አደረጉ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኢትዮጵያ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ኃላፊ በሞቃዲሾ ድንገተኛ ጉብኝት አደረጉ
የኢትዮጵያ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ኃላፊ በሞቃዲሾ ድንገተኛ ጉብኝት አደረጉ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 13.01.2026
ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ኃላፊ በሞቃዲሾ ድንገተኛ ጉብኝት አደረጉ

  አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን፣ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተላከ መልዕክትን፣ ለማድረስ በቪላ ሶማሊያ ከፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሐሙድ ጋር ተገናኝተዋል ሲሉ ባለሥልጣና ገለፀዋል፡፡

ምንም እንኳን የመልዕክቱ ዝርዝር ይዘት ይፋ ባይደረግም፣ ይህ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊ ጉብኝት የተከናወነው እስራኤል ለሶማሊላንድ የአገርነት እውቅና መስጠቷን ተከትሎ በአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ ውጥረት በነገሰበት ወቅት ነው።

ኃላፊው ከሶማሊያ ብሔራዊ መረጃና ደህንነት ኤጀንሲ ዳይሬክተር ማሃድ ሳላድ ጋር በኤጀንሲው ዋና መሥሪያ ቤት መወያየታቸውንም የሶማሊያ ሚዲያ ዘግቧል፡፡

ሁለቱም መንግሥታት ስለ ዛሬው ስብሰባ ውጤት እስካሁን ይፋዊ መግለጫ አልሰጡም።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0