የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ለሁለት የአቪዬሽን ተቋማት የሥራ ፈቃድ ሰጠ
12:08 13.01.2026 (የተሻሻለ: 12:14 13.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ለሁለት የአቪዬሽን ተቋማት የሥራ ፈቃድ ሰጠ
ባለስልጣኑ በኢትዮጵያ አየር ኃይል ስር ለሚገኘው ለከባድ ጥገና ማዕከል እና ለዓለም አቀፍ ካርጎ አቪዬሽን ሰርቪስ (አይፓስ) የአቪዬሽን ጥገና እና የአቪዬሽን ትምህርት የሥራ ፈቃዶችን ሰጥቷል፡፡
ለዓለም አቀፍ ካርጎ አቪዬሽን ሰርቪስ የተሰጠው የሥራ ፈቃድ በአቪዬሽን ማሰልጠኛ አካዳሚ ዘርፍ የተሰማሩ ተቋማትን ቁጥር ወደ አምስት የሚያሳድግ ሲሆን በኢትዮጵያ አየር መንገድ ብቻ ተይዞ የነበረውን የጥገና አገልግልት ለተጨማሪ አንድ ተቋም ክፍት የሚያደርግ ነው።
በሥነ ስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚንስትር ዓለሙ ስሜ እንዳሉት፣ በኢትዮጵያ በበረራ አገልግሎት ላይ የተሰማሩ የግል አቪዬሽን ተቋማት ለአውሮፕላኖች ጥገና አገልግሎት ለማግኘት ወደ ውጭ ሃገራት ሄደው ከፍተኛ ወጪ ያወጡ እንደነበር ጠቁመው ለአየር ኃይል ከባድ ጥገና ማዕከል የተሰጠው የሥራ ፈቃድ ይህን ችግር እንሚቀርፍ ገልጸዋል።
ፈቃድ አሰጣጡ ለጥገና አገልግሎት ይወጣ የነበረውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ከማስቀረት ባሻገር የአየር ትራንስፖርት ዘርፍን ለማስፋፋት እና ለማዘመን ያስቀመጠችውን ዕቅድ እውን ለማድረግ የጎላ አስተዋጽኦ እንደሚኖረውም ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ 12 የግል የአየር በረራ አገልግልት የሚሰጡ ተቋማት በሥራ ላይ እንደሚገኙ በዝግጅቱ ላይ መገለፁን የስፑትኒክ አፍሪካ ጋዜጠና ዘግቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

