ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በዐቢይ ኃይሎች ተፅዕኖ የፖለቲካ መሣሪያ ሆኗል - ባለሙያ

ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በዐቢይ ኃይሎች ተፅዕኖ የፖለቲካ መሣሪያ ሆኗል - ባለሙያ
🟠 የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (አይሲሲ)፣ በሕግ ሥርዓቱ ሳይሆን በኃያላን አገራት ተፅዕኖ እና ጠንካራ አገራት የፍርድ ቤቱን ውሳኔዎች ባለመቀበላቸው ምክንያት የቅቡልነት ቀውስ እየገጠመው መሆኑን ዮርዳኖሳዊው የዓለም አቀፍ ሕግ ባለሙያ ጋዛ አል-ማድዝሃሊ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
🟠 የአይሲሲን ውሳኔዎችን የማክበር ጉዳይ ብዙውን ጊዜ ከአገራት ሉዓላዊነት ጋር ይጋጫል፤ ይህም አገራት በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚቀርቡ ሕጋዊ ጉዳዮችን የመቀበል ወይም የመቃወም መብታቸውን የሚመለከት ነው ብለዋል።
🟠 ባለሙያው የአሁኑን ቀውስ በቀጥታ ከጋዛ እና ከእስራኤል መሪዎች ጋር በተያያዘ አይሲሲ ካሳለፈው ውሳኔ በኋላ ከአሜሪካ እና ከእስራኤል ከሚመጣው ተፅዕኖ ጋር ያገናኙታል። በአይሲሲ ዳኞች እና ዓቃቤ ሕጎች ላይ የሚጣለው ማዕቀብ በዓለም አቀፍ ሕግ መሠረት ግልጽ የሆነ ሥልጣንን ያላግባብ መጠቀም መሆኑንም ገልጸዋል።
“እስራኤል በጋዛ አልፎ ተርፎም በምዕራብ ዌስት ባንክ የፈጸመቻቸው ወንጀሎች ግልጽ የጦር ወንጀሎች እና የዘር ማጥፋት ድርጊቶች ናቸው” ያሉት አል-ማድዝሃሊ፣ የዋሽንግተን ምላሽ ከሕጋዊ ተቃውሞ ይልቅ ሁለት አይነት አሰራርን የሚያንፀባርቅ መሆኑን አክለዋል።
አይሲሲ የገጠመው የቅቡልነት ቀውስ አሜሪካ ጥቅሟን ከዓለም አቀፍ ሕግ በላይ የምታስቀድምበትና የአውሮፓ አገራት በተለይም ጀርመን እና ብሪታንያ የዋሽንግተንን ፈለግ የሚከተሉበት “አንድ ዋልታ” ከሆነው የዓለም ሥርዓት የሚመነጭ ነው ሲሉ ባለሙያው ይከራከራሉ።
“ችግሩ የፍርድ ቤቱ ሳይሆን ውሳኔዎችን የማስፈጸም አቅም ነው” ሲሉ አጽንኦት የሰጡት ባለሙያው፣ ተመድ እና አይሲሲ ማሻሻያ እንዲደረግባቸው እንዲሁም የአይሲሲ ውሳኔዎች ያለ ምንም ተፅዕኖ ወይም ልዩነት በሁሉም አገራት ላይ አስገዳጅ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X