የኢትዮጵያ አትሌቶች በአሜሪካ ቪዛ መከልከል “የስፖርት አፓርታይድ ነው” – የአትሌቲክስ ተንታኝ
18:52 12.01.2026 (የተሻሻለ: 18:54 12.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ አትሌቶች በአሜሪካ ቪዛ መከልከል “የስፖርት አፓርታይድ ነው” – የአትሌቲክስ ተንታኝ
ምርጦቹን በመከልከል ራስን አሸናፊ የማድረግ፣ የውድድሩን ድግስ ማቻቸት እና የራስን ታሪክ በራሰ የመጻፍ አካሄድ መሆኑን በሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ስፖርት ሳይንስ መምህርና የአትሌቲክስ ስፖርት ተንታኝ ኢንስትራክተር መሠረት መንግሥቱ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናገሩ፡፡
የአትሌቲክ ስፖርት አካባቢ ከባድ ፖሊቲካ መኖሩን የጠቀሱት ተንታኙ፣ ለዚህም አደሎዊ ለሆነ አሠራሩ የዓለም አትሌቲክስ ፌድሬሽን ኃላፊነት መውሰድ አለበት ብለዋል፡፡
‘’. . . እንደዚህ አይነት ክልከላዎችን የምትፈፅም ከሆነ፤ ይህ እድል ለምን ለአሜሪካ ይሰጣል? ስፖርት እኮ ገለልተኛ ነው፤ ከፖለቲካ የነፃ ነው ብለው የለም? [...] የሻምፒዮናው አዘጋጅነት ከፍሎሪዳ መነጠቅ ነበረበት ’’ ሲሉ ውሳኔውን ኮንነዋል፡፡
ኢንስትራክተር መሠረት አድሎአዊ ተጽዕኖው በተለያየ መልኩ እንደሚመጣ አስታውሰው የአሁን ደግሞ በቪዛ በኩል መደረጉን ከመጪ ስጋት አክለዋል።
“ነገ ደግሞ በሌላ ነገር ጠብቂ፣ እርግጠኛ ሆኜ ነው የምነግርሽ። [...] ሆን ተብሎ ነው የሚሰጠው ይሄ። ያውቁታል ጠንቅቀው ነው የሚያውቁት። በነገራችን ላይ ጆሯቸውም፣ ዐይናቸውም፣ አፍንጫ የሚያሸቱበትም የት ነው ያለው? ብትይ ኢትዮጵያ እና ኬንያ ውስጥ ነው። በ24 ሰዓት ውስጥ ያለው እንቅስቃሴ ሪፖርት ይደረግላቸዋል።” በማለት የታቀደበት ሴራ መኖሩን የአትሌቲክስ ተንታኙ ገልጸዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው የ2026 የዓለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ልዑክ ከአትላት ወደ ኢትዮጵያ ጉዞውን መጀመሩን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X