ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የናይል ትብብር ማዕቀፍ ስምምነትን እንደትቀላቀል ኢትዮጵያ ጥሪ አቀረበች
18:23 12.01.2026 (የተሻሻለ: 18:24 12.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የናይል ትብብር ማዕቀፍ ስምምነትን እንደትቀላቀል ኢትዮጵያ ጥሪ አቀረበች
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ሀብታሙ ኢተፋ ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የመሰረተ ልማት ሚኒስቴር የተመራ ልዑካን ቡድን ጋር በቢሮአቸው በተወያዩበት ወቅት ጥሪውን አቅርበዋል፡፡
ሚኒስትሩ፣ ኢትዮጵያ ለናይል ወንዝ 96% አበርክቶ እያደረገች ቢሆንም የተፋሰሱ ሀገራትን በመደመር መርህ ለጋራ ብልፅግና እና ጥቅም በጋራ መቆም ይጠበቅብናል እያለች ትገኛለች ብለዋል፡፡
ሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ልዑካን፣ ሚኒስትሩ የተናገሩትን ሐሳብ በመደገፍ ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ ለሚመለከተው አካል እንደሚያሳውቁ መናገራቸውን የኢትዮጵያ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X