የብሪክስ የባሕር ኃይል ልምምድ “ለኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ወደ ባሕር የመመለስ" ጉዞ ትልቅ ምዕራፍ ነው - ባለሙያ
15:26 12.01.2026 (የተሻሻለ: 15:34 12.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የብሪክስ የባሕር ኃይል ልምምድ “ለኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ወደ ባሕር የመመለስ" ጉዞ ትልቅ ምዕራፍ ነው - ባለሙያ
የኢትዮጵያ የባሕር ኃይል በብሪክስ የጋራ ልምምድ ላይ በታዛቢነት መሳተፉ፣ ለሀገሪቱ ስትራቴጂካዊ ጥቅም የሚኖረው ፋይዳ እጅግ የጎላ መሆኑን የቀድሞ የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል አባል ሌፍተናንት ዮሴፍ ሸጋው ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናገሩ፡፡
“ይህ ልምምድ የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ከሌሎች ሀገራት መርከቦችና የአየር ኃይል አካላት ጋር በጋራ የመሥራት፣ መረጃ የመለዋወጥ እና የተቀናጀ ትዕዛዝን የመተግበር አቅሙን (Interoperability) ይፈትሻል፤ ያሳድጋልም።” ብለዋል፡፡
የቀድሞ የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል አባል ሌፍተናንት ዮሴፍ ሸጋው፣ ልምምዱ ኢትዮጵያ ወደፊት በባሕር ሃብት አጠቃቀም ረገድ ለምታደርገው እንቅስቃሴ መሠረት እንደሚጥል ይናገራሉ።
“የሰው ኃይላችን በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለውን ብቃት የሚለካበት እና ኢትዮጵያ በብሪክስ ጥላ ስር ያላትን ስትራቴጂካዊ አጋርነት የምታጠናክርበት ወርቃማ እድል ነው።”
ኢትዮጵያውያን መኮንኖችና ባለሙያዎች እንደ ሩሲያ፣ ቻይና እና ሕንድ ካሉ የዳበረ የባሕር ኃይል ታሪክና ቴክኖሎጂ ካላቸው ሀገራት ልዩ ልዩ ልምዶችን የመውሰድ እድል እንደሚያገኙም ሌፍተናንት ዮሴፍ ጠቁመዋል፡፡
‘’ ... የባህር ላይ ሽብርተኝነትን እና ዝርፊያን የመከላከል ብቃትን ይጨምራል። ሀገሪቱ የንግድ መርከቦቿን ደህንነት ለማስጠበቅ በሚደረገው ዓለም አቀፍ ጥረት ውስጥ የድርሻዋን እንድትወጣ ያዘጋጃታል’’ በማለት የሀገሪቱ እንዲህ ባሉ ትላልቅ ዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ መሳተፏ ዲፕሎማሲያዊ እና ወታደራዊ ተሰሚነቷን ከፍ ያደርገዋል ሲሉም አጠቃለዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X