ኢትዮጵያ ከ10 ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ከኒውክሌር ቴክኖሎጂ ኃይል ማመንጨት እንደምትጀምር ተዘገበ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ ከ10 ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ከኒውክሌር ቴክኖሎጂ ኃይል ማመንጨት እንደምትጀምር ተዘገበ
ኢትዮጵያ ከ10 ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ከኒውክሌር ቴክኖሎጂ ኃይል ማመንጨት እንደምትጀምር ተዘገበ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 12.01.2026
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ ከ10 ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ከኒውክሌር ቴክኖሎጂ ኃይል ማመንጨት እንደምትጀምር ተዘገበ

የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ለመገንባት ከ10 እስከ 15 ዓመታት የሚፈጅ ቢሆንም፣ ኢትዮጵያ እያደረገች ባለው የቅድመ ዝግጅት ፍጥነት ከተጠቀሰው ባነሰ ጊዜ ውስጥ ወደ ሥራ ለመግባት አቅዳ እየሠራች መሆኑን የኢትዮጵያ የኒውክሌር ኢነርጂ ኮሚሽን አስታውቋል።

ኮሚሽኑ ከተቋቋመ በኋላ አስፈላጊ መሠረተ ልማቶችን የመገንባትና ከጥንቃቄና ደኅንነት አኳያ የሚከናወኑ ተግባራትን እየሠራ መሆኑም ተገልጿል።

የኒውክሌር ልማት ፕሮግራሙ የኃይል አቅርቦትን ከአየር ንብረት ጋር በተጣጣመ መልኩ አስተማማኝ ለማድረግ ያለመ መሆኑን የኮሚሽኑን ባለሥልጣን ጠቅሶ የአገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል፡፡

ባለፈው መስከረም የኢትዮጵያ መንግሥት ከሩሲያው መንግሥታዊ የኒውክሌር ኃይል ኩባንያ ሮሳቶም ጋር የኒውክሌር ልማት ፕሮጀክት ስምምነት መፈራረሙ ይታወሳል።

በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምስል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0