ኔቶ አቅሙን እያጣ በመሆኑ የአውሮፓ ሕብረት የመፈራረስ አደጋ ተጋርጦበታል - ተንታኝ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኔቶ አቅሙን እያጣ በመሆኑ የአውሮፓ ሕብረት የመፈራረስ አደጋ ተጋርጦበታል - ተንታኝ
ኔቶ አቅሙን እያጣ በመሆኑ የአውሮፓ ሕብረት የመፈራረስ አደጋ ተጋርጦበታል - ተንታኝ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 12.01.2026
ሰብስክራይብ

ኔቶ አቅሙን እያጣ በመሆኑ የአውሮፓ ሕብረት የመፈራረስ አደጋ ተጋርጦበታል - ተንታኝ

በቅርብ ጊዜያት ውስጥ የአውሮፓ ሕብረት መዋቅር ሊለወጥ እንፍደሚችል ​ቱርካዊቷ የፖለቲካ ተንታኝ ዴኒዝ ዪልዲዝ ለስፑትኒክ ገለፁ፡፡

​ዪልዲዝ እንደሚሉት፣ ጀርመን የኢነርጂ ቀውስን እየታገለች ነው፤ የእንግሊዝ ዘውዳዊ አገዛዝ በቅርቡ ሊያበቃ ይችላል፤ ሃንጋሪ ደግሞ ከአውሮፓውያን የጋራ አጀንዳ ራሷን እያራቀች ትገኛለች።

በእነዚህ ሁኔታዎች ምክንያት የአውሮፓ ሕብረት የመፈራረስ አደጋ እንዳለበትና የኔቶ ጥንካሬም ቀድሞውኑ መዳከሙን አስጠንቅቀዋል።

​ተንታኟ አክለውም፣ እነዚህ በመጀመሪያ እይታ የማይገናኙ የሚመስሉ ሂደቶች ሁሉ አንድ ላይ ተደምረው አንድ ምስል ይፈጥራሉ።  አውሮፓ የቀድሞ "አስተሳሳሪነቷን" እያጣች ነው፡፡ በተጨማሪም የጋራ መረዳጃና የውሳኔ አሰጣጥ ዘዴዎቿ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበላሹ መጥተዋል።

​እያንዳንዱ የአውሮፓ ዋና ከተማ በኃይል፣ በኢኮኖሚ እና በደህንነት ዘርፍ በቅድሚያ ራሱን ለማዳን መሞከር ሲጀምር፣ በሕብረቱ ውስጥ የመነጣጠል ዝንባሌን እንደሚጨምርና በዚህም ኔቶ አንድነቱ ያልተጠበቀና የማይገመት እንዲሆን ያደርገዋል በማለት ዪልዲዝ ሃሳባቸውን አጠቃለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0