የቡርኪና ፋሶ ጉምሩክ በአምስት ቀናት ውስጥ ከ8,000 በላይ ፈንጂዎችን በቁጥጥር ስር አዋለ
19:43 11.01.2026 (የተሻሻለ: 20:04 11.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የቡርኪና ፋሶ ጉምሩክ በአምስት ቀናት ውስጥ ከ8,000 በላይ ፈንጂዎችን በቁጥጥር ስር አዋለ
የቡርኪና ፋሶ ባለሥልጣናት፤ ከፍተኛ መጠን ያለው የፈንጂ ዝውውር ከታህሳስ 26 እስከ 30 ባሉት ቀናት ውስጥ በቁጥጥር ስር ማዋል እንደቻሉ ገልጸዋል።
በሲንካንሴ የድንበር ኬላ በተከናወነው
የመጀመሪያ ኦፕሬሽን፤ የጉምሩክ መኮንኖች በተጓዦች ላይ ባደረጉት ጥብቅ ፍተሻ፤ በጭነት ውስጥ ተደብቀው የተገኙ 872 የፈንጂ ማቀጣጠያ ገመዶችን እና 7 ሺህ የፈንጂ ተጣባቂዎችን ይዘዋል።
ከጥቂት ቀናት በኋላ የክልላዊ ክትትል ዳይሬክቶሬት ተንቀሳቃሽ ተከላካይ ክፍል ባደረገው ሁለተኛ ፍተሻ፤ ተጨማሪ 165 የፈንጂ ተጣባቂዎችን እና 22 የፈንጂ ማቀጣጠያ ገመዶችን በቁጥጥር ስር አውሏል።
በቁጥጥር ስር ከዋሉት ቁሳቁሶች መካከል ከፊሉ ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ እንዲወገዱ ለጦር ኃይሉ የተላለፉ ሲሆን ቀሪው ደግሞ ታሸጎ እንዲቀመጥ ተደርጓል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

1/3
© telegram sputnik_ethiopia

2/3
© telegram sputnik_ethiopia

3/3
© telegram sputnik_ethiopia
1/3
© telegram sputnik_ethiopia
2/3
© telegram sputnik_ethiopia
3/3
© telegram sputnik_ethiopia