ግብፅ የ1.8 ቢሊዮን ዶላር የታዳሽ ኃይል ስምምነቶችን ተፈራረመች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱግብፅ የ1
ግብፅ የ1 - Sputnik አፍሪካ, 1920, 11.01.2026
ሰብስክራይብ

ግብፅ የ1.8 ቢሊዮን ዶላር የታዳሽ ኃይል ስምምነቶችን ተፈራረመች

የኖርዌ የታዳሽ ኃይል አልሚ ስካቴክ በሚንያ ግዛት የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ እና የኃይል ማከማቻ ጣቢያዎችን እንደሚገነባ፤ የግብፅ ካቢኔ መግለጫን በመጥቀስ የአካባቢው የቴሌቪዥን ጣቢያ ዘግቧል።

የኃይል ማመንጫ ጣቢያው በጠቅላላው በ4 ጊጋ ዋት ሰዓት የባትሪ ኃይል ማከማቻ ስርዓቶች በመታገዝ 1.7 ጊጋ ዋት የማመንጨት አቅም እንደሚኖረው ተነግሯል።

ሁለተኛው ፕሮጀክት ደግሞ የቻይናው ሳንግሮው ኩባንያ በሱዌዝ ቦይ ኢኮኖሚ ዞን ውስጥ የኃይል ማከማቻ ባትሪዎችን የሚያመርት ፋብሪካ የሚገነባበት መሆኑን ካቢኔው ገልጿል። ከዚህ ፋብሪካ የሚወጣው ምርት በከፊል ለመጀመሪያው ፕሮጀክት ግብዓት እንዲሆን ታቅዷል።

ግብፅ እስከ እ.ኤ.አ 2030 ድረስ ከአጠቃላይ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦቷ ውስጥ 42 በመቶውን ከታዳሽ የኃይል ምንጮች ለማግኘት አልማ እየሠራች ትገኛለች።

በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0