የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በአፋር ክልል ግዙፍ የፖታሽ ማዕድን ማውጫ ተረከበ
18:51 11.01.2026 (የተሻሻለ: 18:54 11.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በአፋር ክልል ግዙፍ የፖታሽ ማዕድን ማውጫ ተረከበ
ተቋሙ ከአሰብ ወደብ 200 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው የአፋር ክልል ዳሉል ወረዳ 365 ስኩዌር ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የፖታሽ ክምችት የማውጣት መብት አግኝቷል ተብሏል።
የአካባቢው የፖታሽ ክምችት ከ11 እስከ 12 ቢሊዮን ቶን እንደሚገመት የተገለፀ ሲሆን ይህም አካባቢውን በዓለም ላይ ካልተነኩ ሰፊ የፖታሽ ክምችቶች አንዱ ያደርገዋል መባሉን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
ተቋሙ የንግድ የማዕድን ማውጫ ፈቃድ ጥያቄውን በሐምሌ 2017 ካቀረበ በኋላ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባሳለፍነው ሳምንት ፈቃዱን በይፋ እንዳጸደቀ የማዕድን ሚኒስቴርን ያጣቀሰው ዘገባ ጨምሮ ገልጿል።
የፖታሽ ክምችቱ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ከናይጄሪያ ዳንጎቴ ግሩፕ ጋር በሶማሌ ክልል ጎዴ ለሚገነባው ግዙፍ የማዳበሪያ ፋብሪካ ግብዓት እንደሚሆን ይጠበቃል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X