እስራኤል ፍልስጤማውያንን ወደ ሶማሊላንድ በኃይል ለማፈናቀል አቅዳለች - የሶማሊያ መከላከያ ሚኒስትር
18:26 11.01.2026 (የተሻሻለ: 18:34 11.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
እስራኤል ፍልስጤማውያንን ወደ ሶማሊላንድ በኃይል ለማፈናቀል አቅዳለች - የሶማሊያ መከላከያ ሚኒስትር
እስራኤል በሶማሊላንድ የጦር ሠፈር መመስረት ብቻ ሳይሆን “አካባቢውን ልክ እንደ ፍልስጤም መሬቶች ለመያዝ” ማቀዷን አህመድ ሙዓሊም ፊቂ ለመገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል።
ይህ ድርጊት በቀጣይነት “አጠቃላይ የመካከለኛው ምስራቅ ቀጣናን ለማናጋት” መንገድ ይከፍታል ሲሉም ሚኒስትሩ አክለዋል።
ሚኒስትሩ ይህ ሊወሰድ የታሰበው እርምጃ ዓለም አቀፍ ሕግን በከፍተኛ ሁኔታ የሚጥስ እና የሶማሊያን ሉዓላዊነት የሚጋፋ ነው ሲሉ ገልጸውታል።
ፊቂ የእስራኤል መንግሥት “ተገንጣይ” ላሉት ክልል የሰጠውን እውቅና እንዲያነሳ በማሳሳብ፤ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በሉዓላዊ ሀገራት ውስጥ ላሉ አካላት እውቅና ለመስጠት የሚያስችል ሕጋዊም ሆነ ሕገ-መንግሥታዊ ሥልጣን እንደሌላቸው አፅንዖት ሰጥተዋል።
▫ ባለፉት ሁለት ዓመታት ቀደም ሲል በሶማሊላንድ ከተካለሉ አካባቢዎች መካከል ግማሽ ያህሉ በድጋሚ ጉድኝታቸውን ለሶማሊያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ ቢያረጋግጡም፤ እስራኤል ግን ተገንጣይ መሪዎችን እየተጠቀመች ነው ሲሉ ሚኒስትሩ አብራርተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X