የቤት ግንባታ ችግርን የሚቀርፍ አፈርን ከሲሚንቶ ጋር በመቀላቀል ደረጃውን የጠበቀ ቤት ለመገንባት የሚያስችል ጥናት መጠናቀቁ ተገለፀ
17:25 11.01.2026 (የተሻሻለ: 17:34 11.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የቤት ግንባታ ችግርን የሚቀርፍ አፈርን ከሲሚንቶ ጋር በመቀላቀል ደረጃውን የጠበቀ ቤት ለመገንባት የሚያስችል ጥናት መጠናቀቁ ተገለፀ
በሐረሪ፣ በድሬዳዋ እና በጅግጅጋ አካባቢዎች የሚገኘውን አፈር ለቤት ግንባታ በሚውል መልኩ በማዘጋጀት ዙሪያ ከሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የተደረገው ጥናት መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት አስታውቋል።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ታምራት ሙሉ፤ "ቴክኖሎጂው አፈርን ከትንሽ ሲሚንቶ ጋር በመቀላቀል ደረጃውን የጠበቀ ቤት ለመገንባት የሚያስችል ነው" ሲሉ ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ተናግረዋል።
ጥናቱ ሁሉንም የኢንጂነሪንግ መስፈርቶች አሟልቶ በቤተ-ሙከራ ተረጋግጧል የተባለ ሲሆን በአሁኑ ወቅት "ለአካባቢያዊ ችግር አካባቢያዊ መፍትሔ" በሚል ስትራቴጂ ለመጨረሻ ማረጋገጫ ለውይይት መቅረቡ ተመላክቷል።
ግንባታዎች ሙሉ በሙሉ በሲሚንቶ ላይ ብቻ የተንጠለጠሉ እንዳይሆኑ በማድረግ እና የግንባታ ወጪን በመቀነስ ከ6 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ የሐረሪ፣ ድሬዳዋ እና ጅግጅጋ ነዋሪዎች የቤት ግንባታ ችግርን የሚቀርፍ መፍትሔ ይዞ መቅረቡን ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X