ግብፅ እስራኤል ለ "ሶማሊላንድ" የሰጠችው እውቅና ዓለም አቀፍ ሥርዓትን ያናጋል ስትል አስጠነቀቀች
16:55 11.01.2026 (የተሻሻለ: 17:04 11.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ግብፅ እስራኤል ለ "ሶማሊላንድ" የሰጠችው እውቅና ዓለም አቀፍ ሥርዓትን ያናጋል ስትል አስጠነቀቀች
የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብደላቲ፤ ካይሮ የትኛውንም ዓይነት የአንድ ወገን ወይም ሕገ-ወጥ የ "ሶማሊላንድ" እውቅና በጽኑ እንደምትቃወም፤ በእስልምና ትብብር ድርጅት አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አስቸኳይ ስብሰባ ላይ አረጋግጠዋል።
የአፍሪካ ቀንድ ወቅታዊ ተግዳሮቶች፤ ሶማሊያ ተቋሞቿን እንደገና ለመገንባትና የግዛት ቁጥጥሯን ለማረጋገጥ ለምታደርገው ጥረት ዓለም አቀፍ ድጋፍን የሚጠይቅ ነው ብለዋል።
አብደላቲ አክለውም፤ የእስራኤልን ውሳኔ በማውገዝ የሶማሊያን የግዛት አንድነትና ብሔራዊ አንድነት በመደገፍ ጽኑ አቋም ለያዙት ለእስልምና ትብብር ድርጅት አባላት፣ ለአረብ ሊግ እና ለአፍሪካ ኅብረት አድናቆታቸውን ገልጸዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X