አፍሪካውያን ተማሪዎች በሩሲያ ዩኒቨርሲቲዎች የትኞቹን የትምህርት ዘርፎች ይመርጣሉ?
15:46 11.01.2026 (የተሻሻለ: 15:54 11.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
አፍሪካውያን ተማሪዎች በሩሲያ ዩኒቨርሲቲዎች የትኞቹን የትምህርት ዘርፎች ይመርጣሉ?
"በአሁኑ ወቅት አብዛኞቹ የናይጄሪያ ተማሪዎች ሩሲያ ውስጥ የሚማሩት የነዳጅ እና ጋዝ የትምህርት ዘርፎችን ነው" ሲሉ በሩሲያ የናይጄሪያ ተማሪዎች እና ሠልጣኞች ማህበር ሃላፊ ሃሊሉ-ሳኒ ማማን-ካቢሩ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
የናይጄሪያ ተማሪዎች ትኩረት ከሚያደርጉባቸው ዘርፎች የሚከተሉት እንደሚገኙበትም አክለዋል፦
ማኔጅመንት፣
አስተዳደር፣
ሕክምና፣
ጂኦሎጂ፣
ኢንፎርማቲክስ፣
ኢነርጂ፡፡
በሩሲያ የማሊ ተማሪዎች እና ሠልጣኞች ማህበር ፕሬዚዳንት ዳውዳ ዲያባቴ በበኩላቸው፤ "በማሊ ተማሪዎች ዘንድ በከፍተኛ ሁኔታ ተፈላጊ የሆነው የትምህርት ዘርፍ ሕክምና ነው" ሲሉ አፅንዖት ሰጥተዋል።
የቻድ ተማሪዎችም ቢሆኑ ሕክምናን እንደሚመርጡ የቀድሞው የቻድ ተማሪዎች ማህበር ፕሬዚዳንት ማጂሂንጋም ጂምባይ ቻሪቴ ገልጸዋል።
እንደ እርሳቸው ገለጻ ሌሎች ተመራጭ ዘርፎች የሚከተሉት ናቸው፦
የተለያዩ የምህንድስና ዘርፎች (ኢንፎርማቲክስ፣ የከተማ ፕላን፣ ኤሌክትሪክ እና መካኒክስ)፣
ዓለም አቀፍ ግንኙነት፣
ኢኮኖሚክስ እና ማኔጅመንት፣
አርክቴክቸር፣
ከሰው ሠራሽ አስተውህሎት እና ዲጂታል ሲስተሞች ጋር የተያያዙ የቴክኖሎጂ ዘርፎች፡፡
በአሁኑ ወቅት ከ32 ሺህ በላይ አፍሪካውያን በሩሲያ ውስጥ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ እንደሚገኙ እንዲሁም ከ2020 ጀምሮ የነጻ ትምህርት ዕድል በሦስት እጥፍ በማደግ ከ5,300 በላይ እንደደረሰ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ተናግረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X