የቢሾፍቱ አየር ማረፊያን ከነባሩ የቦሌ አየር ማረፊያ ጋር የሚያገናኝ የ38 ኪሎሜትር የፍጥነት መንገድ እንደሚገነባ ተነገረ
14:15 11.01.2026 (የተሻሻለ: 14:24 11.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የቢሾፍቱ አየር ማረፊያን ከነባሩ የቦሌ አየር ማረፊያ ጋር የሚያገናኝ የ38 ኪሎሜትር የፍጥነት መንገድ እንደሚገነባ ተነገረ
ከአዲሱ አየር ማረፊያ ወደ ቦሌ የሚገነባው የፍጥነት መንገድ በእያንዳንዱ አቅጣጫ ስድስት፣ በድምሩ 12 ተሽከርካሪዎችን እንደሚያስተናግድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናግረዋል።
የፍጥነት መንገዱ የአረንጓዴ አሻራ ያሉት፤ በዙርያው ሙሉ በሙሉ አርንጓዴ መልክዐ ምድር የሚታይበት እንደሚሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በአዲሱ አየር ማረፊያ ግንባታ ማስጀመሪያ ሥነ-ሥርዓት ላይ ጠቁመዋል።
በተጨማሪም 38 ኪሎሜትር የሚጠጋ በሰዓት ከ120 እስከ 200 ኪሎሜትር ፍጥነት የመጓዝ አቅም ያለው የባቡር መስመር በሀገር በቀል ኩባንያዎች እንደሚገነባ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልፀዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X