የካሜሩን ክሪቢ የነዳጅ ማጣሪያ ቀድሞ ከተያዘለት የግዜ ገደብ ሁለት ዓመት አስቀድሞ ማምረት እንደሚችል ተነገረ
19:50 10.01.2026 (የተሻሻለ: 07:44 11.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የካሜሩን ክሪቢ የነዳጅ ማጣሪያ ቀድሞ ከተያዘለት የግዜ ገደብ ሁለት ዓመት አስቀድሞ ማምረት እንደሚችል ተነገረ
በመጀመሪያ እ.ኤ.አ በ2028 ሥራ ይጀምራል ተብሎ ታቅዶ የነበረው የነዳጅ ማጣሪያ፤ በ2026 ሁለተኛ አጋማሽ ሥራ ሊጀምር ይችላል መባሉን የካሜሩን የዜና ምንጮች ዘግበዋል።
ሲ-ስታር ፔትሮሊየም በመጀመሪያ በቀን 10 ሺህ በርሜል በማምረት በከፊል ሥራ ለመጀመር፤ በኋላም የማምረት አቅሙን ወደ 30 ሺህ በርሜል ለማሳደግ አቅዷል።
ይህ የመጀመሪያ ምዕራፍ የሀገሪቱን የናፍጣ እና የቤንዚን ፍላጎት 22 በመቶ ያህል ሊሸፍን እንደሚችል ተዘግቧል።
በክሪቢ ወደብ 250 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ማጣሪያ፤ ወደ 300 ሺህ ሜትር ኩብ ሊያድግ የሚችል 250 ሺህ ሜትር ኩብ ነዳጅ የመያዝ አቅም ያለው የማከማቻ ተርሚናልን ያካተተ ሲሆን ግንባታውም 204 ሚሊዮን ዶላር ይፈጃል ተብሎ ተገምቷል።
ይህ ስትራቴጂያዊ ፕሮጀክት የሚከተሉት ጥቅሞችን እንደሚያስገኝ ተጠቅሷል፦
🟠 ካሜሩን በኢነርጂ ዘርፍ ራሷን ለመቻል የምታደርገውን ጥረት መደገፍ።
🟠 ከ7 ሺህ በላይ ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያልሆኑ የሥራ ዕድሎችን መፍጠር።
🟠 ከውጭ የሚገባውን ነዳጅ በ30 በመቶ ይቀንሳል ተብሎ ይጠበቃል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X