ናይጄሪያ በጠለፋ በተጠቁ አካባቢዎች የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን በከፊል ልትከፍት ነው
19:33 10.01.2026 (የተሻሻለ: 19:34 10.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ናይጄሪያ በጠለፋ በተጠቁ አካባቢዎች የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን በከፊል ልትከፍት ነው
ደህንነታቸው በተረጋገጠ አካባቢዎች የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ከጥር 4 ጀምሮ ትምህርት ይጀምራሉ ተብሏል። እንዲከፈቱ የተፈቀደላቸው ትምህርት ቤቶች ይፋዊ ዝርዝርም በዚያው ዕለት ይፋ እንደሚደረግ በናይጄሪያ የኒጀር ግዛት ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።
ትምህርት ቤቶቹ በቅርቡ በተማሪዎች ላይ የተፈጸመውን ተከታታይ የጠለፋ ወንጀል ተከትሎ መዘጋጀታቸው ይታወሳል። ከፍተኛ ስጋት ባለባቸው ቀጣናዎች የሚገኙ የትምህርት ተቋማት ግን ተጨማሪ ማሳሰቢያ እስኪሰጥ ድረስ ተዘግተው እንደሚቆዩ ተገልጿል።
እ.ኤ.አ. በ2025 መገባደጃ በናይጄሪያ በተለይም በኬቢ፣ ቦርኖ እና ኒጀር ግዛቶች ጠለፋ መብዛቱን ተከትሎ ለተማሪዎች ደህንነት ሲባል ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል።
ትምህርት ቤቶቹን በከፊል የመክፈት ውሳኔ ከፀጥታ ግምገማ እና ከፀጥታ ኃይሎች ጋር ውይይት ከተከናወነ በኋላ እንተደላለፈ ተመላክቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X