ከአሜሪካ ጥረት በተቃራኒ ላቲን አሜሪካ ከቻይና ጋር ያላትን ግንኙነት አታቋርጥም - ሪፖርት

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱከአሜሪካ ጥረት በተቃራኒ ላቲን አሜሪካ ከቻይና ጋር ያላትን ግንኙነት አታቋርጥም - ሪፖርት
ከአሜሪካ ጥረት በተቃራኒ ላቲን አሜሪካ ከቻይና ጋር ያላትን ግንኙነት አታቋርጥም - ሪፖርት - Sputnik አፍሪካ, 1920, 10.01.2026
ሰብስክራይብ

ከአሜሪካ ጥረት በተቃራኒ ላቲን አሜሪካ ከቻይና ጋር ያላትን ግንኙነት አታቋርጥም - ሪፖርት

በቬንዙዌላ የተካሄደውን ዘመቻ ተከትሎ አሜሪካ የውጭ ተቀናቃኞቿ ወደ ምዕራቡ ንፍቀ ክበብ እንዲገቡ እንደማትፈቅድ ያስታወቀችው የቻይናን እየጨመረ የመጣ ተፅዕኖ ግምት ውስጥ በማስገባት መሆኑን አንድ የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል።

አሜሪካ በቬንዙዌላ እና በፓናማ የምትወስደው እርምጃ የአካባቢው ሀገራት ከቻይና ጋር ያላቸውን ግንኙነት እንዲያቋርጡ ለማድረግ የታቀደ ጫና መሆኑን ዘገባው አክሎ ገልጿል።

ሆኖም ሚዲያው ያነጋገራቸው ባለሙያዎች፤ ይህ የአሜሪካ አቋም የላቲን አሜሪካ ሀገራትን ከቻይና ጋር ከመተባበር ያግዳቸዋል የሚለው ሃሳብ ያልተረጋገጠ ነው ይላሉ።

ቁልፍ ነጥቦች፦

በቺሊ ዩኒቨርሲቲ ረዳት ፕሮፌሰር የሆኑት አንድሬስ ቦርኬዝ እንደገለጹት፤ ቻይና በ “አዲሱ የሐር መንገድ” ስትራቴጂዋ አማካኝነት ከቀጣናው ሀገራት ጋር የንግድና የኢንቨስትመንት ትስስር በመፍጠር ጠንካራ አቋም ይዛለች።

የቻይና ተሳትፎ እንደ ኢነርጂ፣ ሎጅስቲክ እና ቴክኖሎጂ ያሉ ልዩ ልዩ ዘርፎችን ያጠቃልላል ሲሉ አክለዋል።

የላቲን አሜሪካ ሀገራት ከአንዱ ወገን ጋር ብቻ ከመቆም ይልቅ ከአሜሪካም ሆነ ከቻይና ጋር ያላቸውን ግንኙነት አጣጥሞ ለመቀጠል ዓላማ አላቸው። ስለዚህ ለአሜሪካ ጫና እጅ እንደሚሰጡ የሚያሳይ ምልክት የለም ሲሉ ጠቁመዋል።

የሳውዘርን ካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር ካሮል ዌይዝ በበኩላቸው፤ ሌላ ትኩረት የሚሻው ነጥብ የቻይና የዕለት ተዕለት ተፅዕኖ ነው ብለዋል። ሰዎች ከስማርት ስልኮች እስከ ተሽከርካሪዎች የቻይና ምርቶችን እየገዙ ይጠቀማሉ፤ ይህ ደግሞ በአሜሪካ መግለጫዎች የሚቀየር አይደለም።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0