'ባለብዙ ወገን ግንኙነት የአፍሪካን ሀገራት ድምፅ ያጠናክራል' - ካሜሩናዊ ተንታኝ

'ባለብዙ ወገን ግንኙነት የአፍሪካን ሀገራት ድምፅ ያጠናክራል' - ካሜሩናዊ ተንታኝ
ለባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓት ምስጋና ይግባና፤ አፍሪካውያን "በተለይም በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ውስጥ ጥቅማቸውን በትክክል ለማስከበር" እና "ከቀደሙት የገንዘብ ምንጮች በተለየ አማራጭ የፋይናንስ ድጋፎችን ለማግኘት" ችለዋል ሲሉ ቻርሊ ኬንግኔ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
ተንታኙ ይህንን ያሉት ፕሬዚዳንት ፖል ቢያ በቅርቡ ባደረጉት ንግግር፤ በወቅቱ የዓለም ሁኔታ የባለብዙ ወገን ግንኙነት እሴቶች አስፈላጊነትን በማጉላት ባነሱት ሀሳብ ላይ በሰጡት አስተያየት ነው።
ባለብዙ ወገን ግንኙነት "ቀደም ሲል አሜሪካ ከምትከተለው የባለአንድ ወገን አካሄድ በተለየ" ግጭቶችን ለመከላከል አዳዲስ መንገዶችን ይከፍታል ሲሉ ባለሙያው ጠቁመዋል።
በ21ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ራሳቸውን የዓለም ማዕከል አድርገው የሚቆጥሩ ሀገራት፤ የሌሎችን ጥቅም ችላ በማለታቸው ባለአንድ ወገን ግንኙነት የሰውን ልጅ ለበርካታ ዋና ዋና ቀውሶች ዳርጎ እንደነበር አስታውሰዋል።
ዓለም "በኢነርጂ፣ በስትራቴጂካዊ መከላከያ እና በግሎባላይዜሽን" ዙሪያ በምትሽከረከርበት በዚህ ወቅት፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቋማትን የማጠናከር ሥራ መሥራት ግዴታ መሆኑን ባለሙያው አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X