ዚምባብዌ ትምህርት ቤቶች ከመከፈታቸው በፊት 7,472 መምህራንን ቀጠረች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱዚምባብዌ ትምህርት ቤቶች ከመከፈታቸው በፊት 7,472 መምህራንን ቀጠረች
ዚምባብዌ ትምህርት ቤቶች ከመከፈታቸው በፊት 7,472 መምህራንን ቀጠረች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 10.01.2026
ሰብስክራይብ

ዚምባብዌ ትምህርት ቤቶች ከመከፈታቸው በፊት 7,472 መምህራንን ቀጠረች

የዚምባብዌ መንግሥት፤ በመንግሥትና በግል ዘርፎች የሥራ ዕድል ፈጠራን ከማበረታታት ባሻገር፤ የመምህራንን ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እያሳደገ የትምህርት ጥራትን በማሻሻል ይገኛል።

በየመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ሚኒስቴር የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ታውንጋና ንዶሮ እንደገለፀት፤ ቅጥሩ የሚከተሉትን ግቦች ለማሳካት ታቅዶ የተከናወነ ነው፦

የመምህርና ተማሪ ምጣኔን ማሻሻል፣

የትምህርት ውጤት ማሳደግ፣

የመምህራንን የሥራ ጫና መቀነስ፣

የማኅበረሰብ ተሳትፎን ማጠናከር፣

በትምህርት ተደራሽነት ላይ የሚታዩ ኢ-ፍትሐዊነቶችን መቀነስ።

አዲሶቹ መምህራን በጡረታ ወይም በሞት ምክንያት በለቀቁ መምህራን ምትክ እንዲሁም ቁጥራቸው እየጨመረ የመጣ ተማሪዎችን ለማስተናገድ በተፈጠሩ አዳዲስ የሥራ መደቦች ላይ እንደሚመደቡ ንዶሮ ገልጸዋል።

ዳይሬክተሩ አክለውም፤ መምህራኑ የተሻሻለውን የትምህርት ሥርዓት ተግባራዊ ለማድረግ፣ በአዳዲስ ዕውቀቶችና አመለካከቶች የ21ኛው ክፍለ ዘመን ትምህርት ለመስጠት ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ አብራርተዋል።

የቅጥር ሂደቱ የትምህርት ተደራሽነት ላይ የሚታዩ ልዩነቶችን ለመቅረፍ ያለመ ሲሆን ሁሉም ተማሪዎች ጥራት ያለው ትምህርት እንዲያገኙ ብቁ መምህራን በገጠርና ተጠቃሚ ባልሆኑ አካባቢዎች እንዲመደቡ ይደረጋል ሲሉ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

በሰው ሰራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0