ኢትዮጵያና ኬንያ በ2026 የአፍሪካን የኢኮኖሚ ዕድገት እንደሚመሩ ተመድ አስታወቀ
15:32 10.01.2026 (የተሻሻለ: 15:34 10.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያና ኬንያ በ2026 የአፍሪካን የኢኮኖሚ ዕድገት እንደሚመሩ ተመድ አስታወቀ
በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የ2026 የዓለም ኢኮኖሚ ሁኔታ እና የትንበያ ሪፖርት መሠረት፤ ዘንድሮ የአፍሪካ ኢኮኖሚ 4 በመቶ ያድጋል ተብሎ ይጠበቃል።
ይህም ባለፉት ሁለት ዓመታት ከተመዘገቡት የ3.5 እና የ3.9 በመቶ ዕድገት የተሻለ ውጤት እንደሚሆን የተገለፀ ሲሆን ለዚህ ዕድገት ኢትዮጵያ እና ኬንያ በዋናነት ከፍተኛውን ድርሻ እንደሚይዙ ተመላክቷል።
በ2026 5.8 በመቶ ይደርሳል ተብሎ የሚጠበቀው የምስራቅ አፍሪካ ቀጣና ዕድገት ከአፍሪካ ከፍተኛው ሲሆን የኢትዮጵያ እና የኬንያ የኢኮኖሚ አፈጻጸም፣ የታዳሽ ኃይል መስፋፋት እና የቀጣናዊ ትስስር መጠናከር መነሻ እንደሚሆን ተጠቁሟል።
ከፍተኛ የዕዳ ጫና፣ የምግብ ዋጋ ንረት እና የአጎአ ስምምነት የሚያበቃበት ጊዜ መቃረብ ለአኅጉሪቱ ዘላቂ ልማት ስጋት እንደሆኑ ሪፖርቱ ጠቅሷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X