የድሬ ሼኽ ሁሴን መስጂድን በዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ እና የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ እየተሠራ እንደሆነ ተገለፀ
14:35 10.01.2026 (የተሻሻለ: 14:44 10.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የድሬ ሼኽ ሁሴን መስጂድን በዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ እና የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ እየተሠራ እንደሆነ ተገለፀ
በምስራቅ ባሌ ዞን የሚገኘውን ይህን ጥንታዊ፣ መንፈሳዊ እና ታሪካዊ ስፍራ በዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ ጥረት እየተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳሬክተር ሕይወት ኃይሉ ተናግረዋል።
የቅርሱን ገፅታ መቀየር የሚያስችል የመንገድ፣ የኤሌትሪክ ኃይል እና ንፁህ የመጠጥ ውሃ ተደራሽ ለማድረግ ተግባራዊ እንቅስቃሴ መጀመሩን የሀገር ውስጥ ሚዲያ የአካባቢውን ባለሥልጣን ጠቅሶ ዘግቧል።
የጥንታዊ ኢትዮጵያ የግንባታ ጥበብ ውጤት ማሳያ ነው የተባለው የድሬ ሼኽ ሁሴን መስጂድ፦
በ11ኛው ክፍለ ዘመን የተገነባ፣
የውሃ ኩሬን ጨምሮ በርካታ የጥንታዊ ስልጣኔ መገለጫዎች የሚገኙበት፤
በሙሉ ነጭ ቀለም ያሸበረቁ ሕንፃዎች ያሉት ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X